Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድሮዬን አልደግምም

Deroyien Aldegmem

2013 · ትራክ 6 · 4:10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አላስተያይህም ከሚሆነው ከሁኔታው ጋራ

ከሚመጣው ዳግም ከሚሄደው ከንፋስ ሽውታ

ምክንያቱ አንተ ነህ አንተን የማመልክበት

በቂ ነው መዳኔ ከበቂም በላይ ነው መትረፌ

ኢህን በሥልጣኑ ማድረግ ማን ቻለበት

አይደለም ዎይ ያወጣኸኝ ከባርነት

አይደለም ዎይ የፈታኸኝ ከእስራት

ታዲያ እንዴት ነው መኖሩ

ዳግም ተለይቶ ወጥቶ ከነጻነት

ድሮዬን አልሻም ድሮዬን አልደግምም

እኔ አልመለስም እስር ቤት

እኔ አልመለስም እስር ቤት

አልመለስም እስር ቤት (፫x)

ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመልስ

አልገኝም ኋላዬን ስከልስ

የያዝኩት መንገድ ገብቶኛል

ልክ ነው ማን ያስተኛል

ሕይወት ነው እውነት የሞላበት

የሰላም ነው ቤቱ ያለንበት

እጠራለሁ እንጂ ሌላውን

ያልገባውን ያላየዉን

እኔ አልመለስም እስር ቤት

አልመለስም እስር ቤት (፪x)

እኔ አልመለስም እስር ቤት (፪x)

አልመለስም እስር ቤት (፪x)

እኔ አልመለስም እስር ቤት (፪x)

ዴማስን : ሳልሆን ተላላ

መንገድ ላይ ሳልቀር ከኋላ

ከመቅበዝበዝ ሕይወት ድኛለሁ

ከዓለም ፍቅር ተርፊያለሁ

ዘምራለው ከቶ አልዘፍንም : ቆሜ

ጾሜ ታች አልወርድም እላይ ተሰይሜ

አበራለሁ ገና መዳኔን

ብርቁን ታሪክ የኢየሱሴን

እኔ አልመለስም እስር ቤት

አልመለስም እስር ቤት (፪x)

እኔ አልመለስም እስር ቤት (፪x)

እኔ አልመለስም እስር ቤት (፪x)

አልመለስም እስር ቤት (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ