Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የሮጡለትን ያዩታል

Yerotuleten Yayutal

2013 · ትራክ 3 · 5:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከአንተ በፊት የቆሰሉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ

እንደ እኔና እንደ አንተ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ

ከአንቺ በፊት የተሰዉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ

እንደ እኔና እንደ አንቺ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ

ከእኛ በፊት ብዙ አሉ የተሰዉ ለወንጌሉ

እንደ እኛ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ

ሳይሉ እጅ እግሬን ጨርቄን ማቄን በጽድቅ የኖሩ

በጌታ የተጉ ለጌታ የኖሩ በሰው የተጠሉ

አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ

የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሠማይ

አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት

ሳያዩት ያመኑትን የናፈቁትን

በነፍሳቸው የጨከኑት በሥጋቸው ያከበሩት

አይገኝም አክሊላቸው በሠማይ ነው ክፍያቸው

አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ

ሆነው የባርነት ባሪያ ወጥተው ከሰውነት ተራ

የእኔ የሚሉት የሌላቸው ልሩጥ ለእኔም ማያቃቸው

ለወንጌል የቆሙ ለወንጌል የቀኑ

ገንዘብ የማይደፍራቸው ሰልፍ ብርታታቸው

አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ

የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሠማይ

አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት

ሳያዩት ያመኑትን የናፈቁት

በነፍሳቸው የጨከኑት በሥጋቸው ያከበሩት

አይገኝም አክሊላቸው በሠማይ ነው ክፍያቸው

አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት

ማነው ታዲያ የዘመኔ አርበኛ

ለጌታ ነገር ያልተኛ

ብድራቱን እዚህ ያልተቀበለ

እውነት ለወንጌል የጨከነ

በነጻነት ዘመን ራሱን የሰዋ

ለጥቅም ያልኖረ በእምነቱ የጸና

ማነው የዘመኔ ወንጌል ነጋሪ

በተግባር የታየ የጽድቅ ተባባሪ

ያልሆነ በፍፁም የነጻነት ባሪያ

ከቶ ያልተገኘ እዚህ ሲሉት እዚያ

ማነው የአቋም ሰው ዘመን ተሻጋሪ

ሰልፍ እየበረታ ወንጌሉን ዘማሪ

ማነው የዘመኔ ባለ አክሊል ተረኛ

ለራሱ ያልኖረ ከሥጋው ጠበኛ

ሞትን ጥቅሜ ብሎ በነፍሱ የጨከነ

ግራ ቀኝ ያላየ ለቃሉ የታመነ

ማነው የዘመኔ አርበኛ ማነው

አቤት የሮጡለትም ያዩታል ከወደላይ

የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሠማይ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ