ያለ ምክንያት
Yale Mekniyat
2013 · ትራክ 10 · 5:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስፈራ ስቸር ማልተነፍሰው ሚስጥሬ በዝቷል
እኔ ባልናገር የልብ ወዳጄ የውስጤን ያውቃል
እርሱ እንደሚያውቀኝ ሰው አያውቀኝም እንጂ
መቆም አልችልም እንኳን በንጉሥ በራሴም ደጅ
የምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል
አዝማች · Chorus
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል (፪x)
ፈላጊዬ መሃሪዬ ኢየሱስ ወዳጄ
አይዞሽ የሚለኝ እኔን ሚያበረታኝ
ነው የልብ ወዳጄ ነው ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንዳትወደኝ በመልካምነቴ
ይህ አይደለም ማንነቴ
እንዳትጠላኝ ደግሞ በጥፋቴ
ፍቅር ነህ አያስችልህም አባቴ
ያለ ምክንያት ወደህ በምክንያት አትጠላም
ለምህረትህ ስፍር መለኪያ የለውም
የአንተ ፍቅር መነሺያው ከራስህ
የመውደድ ልብ የማያልቅብህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የእኔ ጌታ
ከወዳጅ ከፍቶ ልጅህ ድርሻዬን ብሎ እርም እንዳላለ
አልመች ቢለው የሸፈተበት አባቴን አለ
አባትነቱን የበደል ብዛት መች ይሽረዋል
ሁልን እረስቶ ደግሞ እንደገና ልጄ ይለዋል
በምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል
የምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል
አዝማች · Chorus
ፈላጊዬ መሃሪዬ ኢየሱስ ወዳጄ
አይዞሽ የሚለኝ እኔን ሚያበረታኝ
ነው የልብ ወአጄ ነው ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ