ወቅት እንዳታበላሽ
Weqt Endatabelash
2013 · ትራክ 11 · 4:05 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ክረምት አልጠብቅም ክረምት ላይ ሆኜ
በጋን እኔ አልሻም በጋ ላይ ቁጭ ብዬ
እሰራለሁ አሁን ስራዬን አለቅም
ዘመኔ ላይ ቆሜ ዘመን አልጠብቅም
ጊዜዬ ነው ወቅቴ ነው ዘመኑ ነው ተራዬ
እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ
ይረዳኛል አምናለሁ የተሰጠኝ ጊዜዬ ነው
እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ
በጊዜ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ትናንት ላልሆነለት ዛሬን አትንፈገው
ከንፈርህን መጠህ ሁድህን አታስብሰው
ተስፋ ለቆረጠው ምክር ካስፈለገ
ዐይኑን ግለጥና አድርሰው ለነገ
ትናንት ዛሬ አይደለም ዛሬ ሌላ ቀን ነው
በትላንቱ ዛሬ ዛሬን ያረሰ ማነው
የመጠውለግ ጸባይ አይሆንም ወዳጄ
ወቅት እንዳታበላሽ ልንገርህ ማልጄ
ቁጥር 2 · Verse 2
በጊዜ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አሁን የዋልንበት ነው ለነገ ተስፋ
የዘራነው ዘር ነው ሚጠብቀን ኋላ
ከሰራነው ዛሬን ከተጋን በበርቱ
እንደርሳለን ካልነው አይቀርም መድረሱ
በጊዜ (፬x)
አዝማች · Chorus
ክረምት አልጠብቅም ክረምት ላይ ሆኜ
በጋን እኔ አልሻም በጋ ላይ ቁጭ ብዬ
እሰራለሁ አሁን ስራዬን አለቅም
ዘመኔ ላይ ቆሜ ዘመን አልጠብቅም
ጊዜዬ ነው ወቅቴ ነው ዘመኑ ነው ተራዬ
እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ
ይረዳኛል አምናለሁ የተሰጠኝ ጊዜዬ ነው
እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ
በጊዜ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ