ፍሰሃዬ
Fesehayie
2013 · ትራክ 9 · 4:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ
የምፈልገው ደስታ ጋራ አልደርስም
ስደርስበት ይቀልብኛል
ሳልጠግበው ይሰለቸኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
የእኔ ክፍተት ሌላ ነው
ብርም ወርቅም አይደለም
ኢየሱስ ነው ረሃቤ
መንፈስ ነው ጥጋቤ
በህልውናህ ሥር መሆን
በአንተ መኖር ውሎ ማደር
በመገኘትህ የታሰበ ሰዉ
ምነኛ የታደለ ነው
አዝማች · Chorus
አስበኝ የእኔንም በህልውናህ
በሚያጽናናው በመንፈስህ
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ
ክብርህን ማየት ነው መሻቴ
ትርጉም ለጠፋው ሕይወቴ
ምላሽ ሲታጣ ከሞላው ቤቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለሞኖር ስዝል ሲደክመኝ
ባዶነቴ ሲጮህብኝ
የእኔ ክፍተት ሌላ ነው
ያለኝ ነገር አይደለም
ኢየሱስ ነህ ረሃቤ
መንፈስው ነው ጥጋቤ
በህልውናህ ሥር መሆን
በአንተ መኖር ውሎ ማደር
አዝማች · Chorus
በመገኘትህ የታሰበ ሰዉ
ምነኛ የታደለ ነው
አስበኝ የእኔንም በህልውናህ
በሚያጽናናው በመንፈስህ
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ
ክብርህን ማየት ነው መሻቴ
ቁጥር 4 · Verse 4
ህልሜ አንተን ማየት በኑሮዬ
ህልሜ አንተን ማየት ነው ጉጉቴ
የደስታዬ ልክ ሰላሜ እርካታዬ
ጥግ ፍስሃዬ ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ
ክብርህን ማየት ነው መሻቴ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ