ቤተ ሰሪ
Biete Seri
2013 · ትራክ 8 · 4:31 · አማርኛ
ባማረ ባጌጠ ቤት ውስጥ ተሰይሚያለሁ
በተዋበ ህዝብ ተከብቢያለሁ
ዙሪያዬን የማየው ሁሉ ለዓይን ይስባል
እኔ ግን ታምሜ ውበቴ ጠፍቶኛል
ከቤትህ ውስጥ እያለሁ እኔ ጐድያለሁ
ለሚያየኝ ለስሙ እኔ እንዳለሁ አለሁ
ቤትህን ሲሞላው ዕልልታና ሆታ
እኔን የሚያውከኝ የነፍሴ ጭንቀቷ
የአንተ ቤት እኔ ነኝ የእኔ ቤት ሌላ ነው
ቤተ ሰሪው በዝቶ መላ የሚለኝ ማነው
ቀርበህ ሳለህ ከደጅ ልትመጣ ወዳጄ
እንዴት ይሆን የማይህ እሩቅ አገር ሄጄ
ያዳራሹ ውበት እኔን ሸፍኖኛል
ግዑዝ ከእኔ በልጦ አልፎ ይኮንነኛል
በጌጥ የታጀበ ቤቱ ተሰርቶ አልቆ
ልብ ሁሉ በእጁ ነው የእኔን ቦታ ወስዶ
ይበል እርሱም ይመር ቦታም አይጥበበን
ግን ለታደሰ ቤት ምነው አጉል አጉል ሆነ
እኔ ካልተደስኩኝ ካልሆንኩኝ እንደ ቤቱ
ትርጉም የለሽ ኑሮ ድካም ነው ለከንቱ
ቀኑ ቀርቧል እያልን ፍጻሜ የዘመን
ከንቱ ቤት ስንሰራ ዘለዓለሙን ትተን
ተላልፈን እንዳንቀር አቤቱ አደራ
የተጣልን እንዳንሆን እንደነበርን ሥምህን ስንጠራ
ሥምህን ስንተጠራ ሥምህን
አደራ የነበርን
ሥምህን ስንጠራ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ