Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በሕይወቴ ዘመን

Beheywetie Zemen

2004 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሕይወቴ ዘመን (፰x)

አልተውከኝም ፈጽሞ አልረሳኸኝም (፪x)

ለአንድ አፍታ አልረሳኸኝም (፪x)

እጅ ጭነህ መርቀኸኛል ተባረክ ብለህ

ለጠላቴ መልስን ሰጠኸው አትንካው ብለህ

እልፍ ስል የበረከት ምንጭ ያጋጥመኛል

ገና ሳልደርስ ስራዬን ሰርተህ ጠብቀኸኛል

ጠብቀኸኛል (፬x)

አቤት ያንተስ ነገር ስንቱ ይነገር

አቤት ያንተስ ስራ ስንቱ ይወራ (፪x)

በሕይወቴ ዘመን (፰x)

አልተውከኝም ፈጽሞ አልረሳኸኝም (፪x)

ለአንድ አፍታ አልረሳኸኝም (፪x)

ስላለፈው ልቤ ሲነሳ ሊያመሰግንህ

በመንገዴ ፈጥረህ ጠበቅከኝ ሌላ ተዓምር

ፍጥረት ሁሉ እጁን ባፉ ላይ እስኪጭን ድረስ

በሩቅ በቅርብ ተዓምር ተባለ ሆነኸኝ ሞገስ

ሆነኸኝ ሞገስ (፬x)

አቤት ያንተስ ነገር ስንቱ ይነገር

አቤት ያንተስ ስራ ስንቱ ይወራ (፪x)

በሕይወቴ ዘመን (፰x)

አልተውከኝም ፈጽሞ አልረሳኸኝም (፪x)

ለአንድ አፍታ አልረሳኸኝም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ