Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ውበትህ ከሰው ልጆች

Webetih Kesew Lejoch

2004 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል

ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል

ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል

እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል

እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (፬x)

ካጠገቤ ቆመህ አበርትተኛል

ከወዳጅም ወዳጅ ወዳጅ ወዳጅ ሆነኸኛል

መደገፍ አንተን ነው መታመን ባንተ እንጂ

ሁሉን እየረታህ ሆንክልኝ ሞገስ

ሆንክልኝ ሞገስ (፪x)

ሆንክልኝ ብቃት (፪x)

ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል

ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል

ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል

እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል

እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (፬x)

ካቻምናን አለፍኩኝ ባንተ በመደገፍ

ዘንድሮን አልሰጋም ስለሆንከኝ ሞገስ

ደስታ የኔ ነው ለቅሶ ለጠላቴ

ይሄንን ያረገው ከፍ ይበል አባቴ

ከፍ ይበል አባቴ (፬x)

ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል

ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል

ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል

እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል

እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (፬x)

ማንንስ እረስተህ ማን ጥለህ ታውቃለህ

ይልቁን ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ ታደርጋለህ

ደካማው በረታ ቆመ በእግሮቹ

ታሪክ ተለወጠ እያየ ጠላቱ

እያየ ጠላቱ (፬x)

ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል

ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል

ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል

እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል

እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ