Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው

Egziabhier Lenie Leyu New

2004 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሰማዩ ስፍራ በክብር ያለው

እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (፪x)

እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (፪x)

ሰማያትን በሃይሉ ያጸና

በምክሩም ግሩም ነው እሱ ገናና

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም ለዘላለም (፪x)

በሰማዩ ስፍራ በክብር ያለው

እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (፫x)

እስረኛውን የፈታ ያከበረ

ምስኪኑን ሰው በከፍታ ላይ ያኖረ

የባርነትን በትር የሰበረው እግዚአብሔር ነው (፪x)

በሰማዩ ስፍራ በክብር ያለው

እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (፫x)

እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ

ጨለማውን የለየ ቀኑን ብርሃን ይሁን ያለ

ዙፋኑ በሰማይ ነው በሰማይ ነው ኦሃሃሃ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው (ያለ ማነው) (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ