ልቤን ጣልኩ
Lebien Talkut
2004 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልቤን ጣልኩት በአንተ ላይ እኔ አልሰጋም አሁንማ
እኔስ አለኝ አለኝ ወዳጅ የማይጥለኝ የማይከዳ (፪x)
በቁጥር ተቆጥሮ ይሄ ነው አይባልም
አንተ ለኔ ያረግከው ሚዛን አይለካውም (፪x)
አለኝ ወዳጅ ብዬ ሙሉ አፌ ቢያወራ
እኔስ ኮራሁብህ አምላክ የለኝ ሌላ (፪x )
አለኝ ወዳጅ ብዬ (አለኝ ወዳጅ ብዬ)
ሙሉ አፌ ቢያወራ (ቢያወራ ቢያወራ)
እኔስ ኮራሁብህ (ኮራሁ) አምላክ የለኝ ሌላ
አዝማች · Chorus
ልቤን ጣልኩት በአንተ ላይ እኔ አልሰጋም አሁንማ
እኔስ አለኝ አለኝ ወዳጅ የማይጥለኝ የማይከዳ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተደላድያለሁ በርሱ ተወድጄ
ዝማሬ ብቻ ነው የሞላው በአፌ (፪x)
ከእንግዲህ ወዲያ ልቤ አይገባም ስጋት
ለሰው የሚያዝነው ሆኖልኛል አባት (፪x)
ከእንግዲህ ወዲያ (ከእንግዲህ ወዲያ)
ልቤ አይገባም ስጋት (አይገባም አይገባም)
ለሰው የሚያዝነው (ኦ) ሆኖልኛል አባት (፪x)
አዝማች · Chorus
ልቤን ጣልኩት በአንተ ላይ እኔ አልሰጋም አሁንማ
እኔስ አለኝ አለኝ ወዳጅ የማይጥለኝ የማይከዳ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ