Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

Mesfin Gutu/Teshager Yalew/Ante Yenie

2004 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ

ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ

በጨለማዬ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ

ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (፪x)

ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (፪x)

ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (፪x)

ተማመለህ እኮ ነው የኔ ጌታ

በጭንቅ የወለድከኝ በጎልጎታ

እድሜዬን በሙሉ ሰጥሃለሁ

ዘላለም ለቃልህ እገዛለሁ እገዛለሁ

ታዲያ ልዘምር እንጂ ልቀኝ እንጂ

ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ

ታዲያ ታዲያ (፪x)

እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል (፬x)

ማንጋት ልማድህ ነውና

ማንሳት ልማድህ ነወና

ማክበር ልማድህ ነወና

ማስዋብ ልማድህ ነውና

ውዴ የኔ ነው እኔም ደግሞ የእርሱ ነኝ የየሱስ ነኝ (፪x)

ማንም አይገባም በመሀላችን

ጉድለት የሌለበት ነው ፍቅራችን

ጊዜም ሁኔታም አይሽረዉም ለኔስ ኢየሱሴ ልዩ ነዉ ልዩ ነዉ (፪x)

ታዲያ ልዘምር እንጂ ልቀኝ እንጂ

ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ

ታዲያ ታዲያ (፪x)

አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ

ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ

በጨለዬ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ

ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (፪x)

ትምክህቴ ኩራቴ የማምለጫ አለቴ፣

አንተ አይደለህም ወይ እውነተኛ ወዳጄ

ትምክህቴ ኩራቴ የማምለጫ አለቴ፣ አንተ አይደለህም ወይ እውነተኛ አባቴ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ