አባት አለኝ
Abat Alegn
2004 · ትራክ 12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማዕበሉን በስልጣን የሚገስጽልኝ
ዞር በል የሚልልኝ
አባት አለኝ እኔ አባት አለኝ (፪x)
ረዳት አለኝ እኔ ረዳት አለኝ (፪x)
ከእናት ካባቴም በላይ ለኔ ራርተህ ስላየሁ (አሃሃ አሃ)
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም እላለሁ
ስደክም አበርትተህ ራሴን በዘይት ቀባህ (አሃሃ አሃ)
ጽዋዬም ተረፈልኝ ኢየሱስ ክብርህ ይስፋ
ጌታ ክብርህ ይስፋ ውዴ ክብርህ ይስፋ (፪x)
ሰው ቢጥል እግዚአብሔር ያነሳል (ሰው ቢጥል)
ሰው ቢጥል እግዚአብሔር ያነሳል
ከብሮ ያከብራል ከፍ ያደርጋል
ሰው ቢጥል እግዚአብሔር ያነሳል (ሰው ቢጥል) (፪x)
እንቅልፍ እንደያዘው እንደተኛ ሰው (፪x)
መስሎኝ ነበር እኔስ ግድ ማይለው (፪x)
ኧረ ይሄስ ሰው ሃይለኛ ነው ተነሳና ዞር በል አለው
ኧረ ይሄስ ሰው ሃይለኛ ነው ተነሳና ጸጥ በል አለው
አዝማች · Chorus
ማዕበሉን በስልጣን የሚገስጽልኝ
ዞር በል የሚልልኝ
አባት አለኝ እኔ አባት አለኝ (፪x)
ረዳት አለኝ እኔ ረዳት አለኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የምስኪን ወዳጅ ሆነህ በጐጆዬ ውስጥ ገባህ (አሃሃ አሃ)
የዘመመው ቤቴ ይኸው ባንተ ቀና
ታዲያ ልዘምር እንጂ ለምን ላጉረምርም (አሃሃ አሃ)
በጐጆዬ ውስጥ ያለው ኢየሱስ ይክበር ውድዬ ይክበር
ጌትዬ ይክበር ወድዬ ይክበር
አዝማች · Chorus
ማዕበሉን በስልጣን የሚገስጽልኝ
ዞር በል የሚልልኝ
አባት አለኝ እኔ አባት አለኝ (፪x)
ረዳት አለኝ እኔ ረዳት አለኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ