ትዝ ይለኛል
Tez Yelegnal
2004 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ
ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ
በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ
ታሪኬን ለውጠህ ፣ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማን ፣ ኧረ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (፪x)
ማን ፣ ኧረ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተማመለህ እኮ ነው የኔ ጌታ
በጭንቅ የወለድከኝ በጎልጎታ
እድሜዬን በሙሉ ሰጥሃለሁ
ዘላለም ለቃልህ እገዛለሁ ፣ እገዛለሁ
ታዲያ ፣ ልዘምር እንጂ
ልቀኝ እንጂ
ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ
ታዲያ ታዲያ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል (፬x)
ማንጋት ልማድህ ነውና ፣ ማንሳት ልማድህ ነወና
ማክበር ልማድህ ነወና ፣ ማስዋብ ልማድህ ነውና
ውዴ የኔ ነው እኔም ደግሞ የእርሱ ነኝ የየሱስ ነኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ማንም አይገባም በመሀላችን
ጉድለት የሌለበት ነው ፍቅራችን
ጊዜም ሁኔታም አይሽረዉም ለኔስ ኢየሱሴ ልዩ ነዉ ፣ ልዩ ነዉ
ታዲያ ፣ ልዘምር እንጂ
ልቀኝ እንጂ
ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ
ታዲያ ታዲያ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ
ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ
በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ
ታሪኬን ለውጠህ ፣ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ