Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኧረ ስንቱ ታለፈ

Ere Sentu Talefe

2004 · ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኧረ ስንቱ ስንቱ ስንቱ ስንቱ ታለፈ

ኢየሱስ እየቀደመ ወዳጄ እየቀደመ

ውድዬ እየቀደመ (፪x)

ስንቱን ተራራ ባንተ አለፍኩኝ

ስንቱን ሸለቆ ውሃ ሞላኸው

ጌታዬ ባንተ ሁሉ ሆነልኝ

ክብር ምስጋና ላንተ ይድረስህ (፪x)

በሕይወቴ በኑሮዬ ጣልቃ እየገባህ

ጣልቃ እየገባህ ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀና

ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀና (፪x)

በአምላኬ ክንዱ ላይ ተደግፌ

በርሱ ደግነት አምናን አልፌ

ዘንድሮን አየሁ ጌታን ታምኜ

ላከብረው መጣሁ ሁሉንም ትቼ (፪x)

በሕይወቴ በኑሮዬ ጣልቃ እየገባህ

ጣልቃ እየገባህ ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀናህ

ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀናህ (፪x)

ማዕረጌ ነህ ማዕረጌ ነህ

ሁሉን ያለፍኩብህ ሁሉን ያለፍኩብህ

ሁሉን ያለፍኩብህ ሁሉን ያለፍኩብህ (፪x)

አምላኬ አምላኬ አምላኬ አምላኬ

አምላኬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ

ጌትዬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ

ውድዬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ

ኢየሱስ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ (፪x­)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ