በርታ ጽና
Berta Tsena
2010 · ትራክ 8 · 7:01 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ሂድ (፮x)
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ቁጥር 1 · Verse 1
ጉልበት ዝሎ አቅም ሲከዳ
ተስፋ አትቁረጥ ዐይንህን አንሳ
ድካምህን ለእርሱ ንገረው
ይረዳሃል የታመነ ነው
ሰውን ጥሎ ፈጽሞ አያውቅም
እዛው ሆነህ ጠብቀህ ዛሬም
ሊጐበኝህ እርሱ ሲመጣ
ምርጫ አትውሰድ ከቶ እንዳያጣህ
አዝማች · Chorus
አንተ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ሂድ (፮x)
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ቁጥር 2 · Verse 2
አየለብኝ ወጀቡ በእኔ
ግራ ገባኝ ዛለ ጉልበቴ
አቅም አጣሁ ከእንግዲህ በቃ
ጌታን ብዬ ምንስ ሊመጣ
የምታየው ተስፋ አስቆራጭ
የምጸማው ፍፁም ማይመች
ግድ የለህም ምጻቱ ቀርቦ
አትመለሰ ግባ በቶሎ
አዝማች · Chorus
አንተ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ሂድ (፮x)
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ቁጥር 3 · Verse 3
የሙሽራው መምጫው ቀርቧል
ሩቅ አይደለም ከበርህ ደርሷል
ያለ ጊዜህ ዘይት ጨርሰህ
እንዳያጣህ ከደጃፍ ወጥተህ
ይልቅ ንቃ ይሙላ ዘይትህ
የመክበሪያ ደርሷል ሰዓትህ
ልትደምቅ ከእርሱ ጋራ
አይደነጋግዝ መብራትህ ይብራ
አዝማች · Chorus
አንተ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ሂድ (፮x)
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ይመጣል ሊያሳርፍህ ተግተህ በስፍራህ
ቁም ዛሬም ድል አለና አትድከም በርታ ጽና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ