ግን እርሱ
Gen Esu
2010 · ትራክ 13 · 4:45 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የኪዳን ልጅ ኪዳን ያለው
የተስፋ ዘር ተስፋ ያለው (፪x)
አይጠፋም ይለመልማል
ገና ምድርን ይወርሳል (፪x)
የአብርሃም ዘር ብዛ ያለው
ውረስ ያለው ቃል የሰጥው
ጋሻ ሆኖት ከለላው
በባዕድ ምድር ላይ መራው
አዝማች · Chorus
ግን እርሱ
አይጠፋም ይለመልማል
ገና ምድርን ይወርሳል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከሰማያት የወረደው
የሰው ልጅን ከፍርድ ያዳነው
ጠላቶቹ እንኳን ቢዋሹ
የመረጣቸው ቢሸሹ
አዝማች · Chorus
ግን እርሱ
አይጠፋም ይለመልማል
ገና ምድርን ይወርሳል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በህልሞቹ የተገፋው
በጉድጓድ ውስጥ የተጣለው
አውሬ በላው ሞቷል በቃ
ባለራዕዩ ምን ሊያመጣ
አዝማች · Chorus
ግን እርሱ
አይጠፋም ይለመልማል
ገና ምድርን ይወርሳል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የኪዳን ልጅ ኪዳን ያለው
የተስፋ ዘር ተስፋ ያለው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አይጠፋም ይለመልማል
ቁጥር 6 · Verse 6
ገና ምድርን ይወርሳል (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ