ሥጋቴ ኧረ ለምኔ
Segatie Ere Lemenie
2010 · ትራክ 6 · 3:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለምንስ እፈራለሁ ኧረ ለምን እሰጋለሁ
ታዲያ ለምን እፈራለሁ እኮ ለምን እሰጋለሁ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከእኔ ጋራ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
አይተወኝ እሱ ታማኝ ነው
ሥጋቴ ኧረ ለምኔ
ተዋጊው እያለ ጐኔ
ዘለዓለሜን ይዞታል ከቶ አትፍራ ብሎኛል
አሳርፎኝ በጉያው ስር ልምን ልፍራ እንዴት ልሸበር
በእጁ መዳፍ ቀርጾኛል አበጃጅቶ ሰርቶኛል
አንተ የእኔ ብሎኛል ሥጋት የለኝ አሳርፎኛል
አዝማች · Chorus
አምላኬ/የጠራኝ ከእኔ ጋራ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
አይተወኝ እሱ ታማኝ ነው
ሥጋቴ ኧረ ለምኔ
ተዋጊው እያለ ጐኔ (፪x)
የእኔ ነገር በእጁ ላይ ነው
ሊያደርገው የታመነ ነው
አላማዉም ከእንግዲህማ
ቀን ቆጥሯል እሱ ሊመጣ
በጊዜው ሁሉ ሆኖ
ነገሬ በጌታ ሰምሮ
አያለሁ ፍርሃቴ ይብቃ
ቃል ወጥቷል ከቸሩ ጌታ
ቃል እያለኝ ለምን እፈራለሁ
የልጅነት ስልጣን የእኔ ነው
ወጀቡንም በድል አዘዋለሁ
አትፍራ ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋራ ነው
በቃ ልረፍ ከእንግዲህ ሳልሰጋ
የታምንኩት አለ ከእኔ ጋር
ሁሉን ትቼ ሁሉን ለእርሱ ጥዬ
ያለፍርሃል ልኑር . (1) .
አዝማች · Chorus
የጠራኝ/አምላኬ ከእኔ ጋራ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
አይተወኝ እሱ ታማኝ ነው
ሥጋቴ ኧረ ለምኔ
ተዋጊው እያለ ጐኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ