ለእኔ ነው
Lenie New
2010 · ትራክ 12 · 5:57 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ነው መንክራተቱ
ቁጥር 1 · Verse 1
መስቀል ላይ ውሎ መሞቱ
ያኔ የፈሰሰው ደሙ
አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ
እንደሚታረድ በግ ዝም ያለው
ግርፋት ስቃዩ ለእኔ ነው
ሞቴን የሞተልኝ በጐልጐታ
ውርደቴን ተዋርዶ ክፉን መታ
በሕይወት አለሁኝ ዛሬም በዚህ ጌታ
አዝማች · Chorus
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ነው መንክራተቱ
ቁጥር 2 · Verse 2
መስቀል ላይ ውሎ መሞቱ
ያኔ የፈሰሰው ደሙ
አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ
ክቡር ሆኖ ሳለ የከበረ
ጌታዬ ስለእኔ ራሱን ጣለ
እርቃኑን ሰቀሉት በእንጨት ላይ
ሃፍረቴን ሸፈነው እርሱ ሊታይ
ዝቅ አለ ወረደ ያ ኤልሻዳይ
አዝማች · Chorus
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ነው መንክራተቱ
ቁጥር 3 · Verse 3
መስቀል ላይ ውሎ መሞቱ
ያኔ የፈሰሰው ደሙ
አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ
ስለእኔ ያለው ፍቅር ስለልጁ
ነፍሱን እስከመስጠት ነበር እርሱ
የእኔን በደል ጌታ ተሸከመ
ተራራውን ወጣ ብዙ ደከመ
ያኔ ቀራንዮ ሁሉ ተፈጸመ
አዝማች · Chorus
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ነው መንክራተቱ
ቁጥር 4 · Verse 4
መስቀል ላይ ቅሎ መሞቱ
ያኔ የፈሰሰው ደሙ
አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ