Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክርስትና

Kerestena

2010 · ትራክ 4 · 5:38 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዋጋ (፫x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና

ይታለፋል ይሁን ከጌታ ጋር

የተዘጋጀልኝ ታላቅ ክብር

መኖር ከኢየሱስ ጋር ክርስትና

መጨረሻው ሲያምር ክርስትና (፪x)

መጨረሻው ሲያምር

ታማኝ ሰው ሆኜለት ፈቃዱን ፈጽሜ

ማለፍ እፈልጋለሁ በምድር እስካለሁ እኔ

ዋጋ ቢያስከፍለኝ ጨክኜ አልፋለሁ

ይረዳኛል ጌታ ያየልኝ ክብር ነው

ዋጋ (፫x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና

መቼ እንደዋዛ ይኖርና

ክብር ዋጋ ያለው እርሱ የሞተለት

አይደለም ሃይማኖት ክርስትና

አለው ሽልማት ክርስትና (፪x)

አለው ሽልማት

እሱን እያየሁኝ ሩጫውን እሮጣለሁ

በእርግጥም አክሊሌን ከእጁ እረከባለሁ

ውጣ ውረዱ ብዙ ቢሆንም መከራ

ፍሬው ያማረ ነው እጅግ የሚያኮራ

ዋጋ (፫x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና

ይታለፋል ይሁን ከጌታ ጋር

የተዘጋጀልኝ ታላቅ ክብር

መኖር ከኢየሱስ ጋር ክርስትና

መጨረሻው ሲያምር ክርስትና (፪x)

መጨረሻው ሲያምር

ሃሳቡን ሃሳቤ አድርጌ ልቀበል

በሞቴም የእርሱን ሞት ደግሞ እንድመስል

ስጋን እስከ መሻቱ??? መስቀል ላይ ተሰቅዬ

ልከተለው ወሰንኩ ያዋጣኛል ብዬ

ዋጋ (፫x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና

መቼ እንደዋዛ ይኖርና

ክብር ዋጋ ያለው እርሱ የሞተለት

አይደለም ሃይማኖት ክርስትና

አለው ሽልማት ክርስትና (፪x)

አለው ሽልማት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ