ጉያህ ስር ነኝ
Guyah Ser Negne
2010 · ትራክ 10 · 6:20 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በልዑል መጠጊያ የሚኖር
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ነህ መሽሸጊያዬ ነህ
ከሌሊቱ ግርማ ድኛለሁ
ጉያህ ስር ነኝ በአንተ አምልጫለሁ
ከአደጋና ከቀትር ጋኔን
አሳለፍከኝ ይዘኀው እጄን
ቁጥር 1 · Verse 1
በእርሱ ተማምኖ ለሚመካበት
አለልኝ ብሎ ለታመነበት
ያወጣል እንጂ ከቶ እርሱ አይጥልም
እንደሰው አይደል ፈጽሞ አይዋሽም
በእጁ ቀርጾ እሱ ለያዘው የጠበቀ ዋስትና አለው (፪x)
አዝማች · Chorus
በልዑል መጠጊያ የሚኖር
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ነህ መሽሸጊያዬ ነህ
ከሌሊቱ ግርማ ድኛለሁ
ጉያህ ስር ነኝ በአንተ አምልጫለሁ
ከአደጋና ከቀትር ጋኔን
አሳለፍከኝ ይዘኀው እጄን
ቁጥር 2 · Verse 2
ከክንፍይ በታች ለተማመነ
ሌላውን ትቶ እርሱ አለኝ ላለ
ጽኑ መኩሪያ ነው የማይበገር
ሁኔታን አይቶ የማይቀየር
ጉያው አድርጐ አቅፎ ያሳልፋል
ትቶ አይሸስም ይልቅ ያቀርባል (፪x)
አዝማች · Chorus
በልዑል መጠጊያ የሚኖር
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ነህ መሽሸጊያዬ ነህ
ከሌሊቱ ግርማ ድኛለሁ
ጉያህ ስር ነኝ በአንተ አምልጫለሁ
ከአደጋና ከቀትር ጋኔን
አሳለፍከኝ ይዘኀው እጄን
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስፈራው
ከጨለማው ገዢ ከማይራራው
ጋርዶ ሸሽጐ ነፍሴን የአዳነው
ልጁ ለሆኑት ደራሽ የሆነው
ቢደገፉት የማያሳፍር
አርፌያለሁ በእርሱ ጥላ ስር (፪x)
አዝማች · Chorus
በልዑል መጠጊያ የሚኖር
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ነህ መሽሸጊያዬ ነህ
ከሌሊቱ ግርማ ድኛለሁ
ጉያህ ስር ነኝ በአንተ አምልጫለሁ
ከአደጋና ከቀትር ጋኔን
አሳለፍከኝ ይዘኀው እጄን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ