ተመችቶኛል
Temechetognal
2010 · ትራክ 1 · 5:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አለኝ (፫x) ሚወራ ዛሬ
አለኝ አለኝ ሚወራ ዛሬ
እኔ አለኝ (፫x) ሚወራ ዛሬ
አለኝ አለኝ ሚወራ ዛሬ
አቤት አቤት ስራው
አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት
አዝማች · Chorus
ፍቅሩ በዛ ለእኔ ያደረገው መድህኔ
አላስችል አለኝ ላውጣ
ምላሽ ይሆን ዘንድ ላውራ
ይሄ ደጉ አምላክ ደጉ
ዝም አያሰኝም ፍቅሩ
አትታዘቡኝ ልጩህ ተመችቶኛል ደጁ
ተመችቶኛል ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ደጁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተመችቶኛል (፫x) ደጁ ተመችቶኛል
ተመችቶኛል (፫x)
ምርጫዬ ሆኗል ከደጃፉ ስር
ግራ ቀን አላይ ምቹ ነው ፍቅርህ
ቀን አይቶ አይገፋም አይለወጥም
በሁኔታዎች አይቀየርም
አለኝ ያልኩት ሲጠፋ ተስፋ ያደረኩት ሲከዳ
ኢየሱሴ ብቻውን ያለአጋዥ ረዳኝ
አዝማች · Chorus
ፍቅሩ በዛ ለእኔ ያደረገው መድህኔ
አላስችል አለኝ ላውጣ
ምላሽ ይሆን ዘንድ ላውራ
ይሄ ደጉ አምላክ ደጉ
ዝም አያሰኝም ፍቅሩ
አትታዘቡኝ ልጩህ ተመችቶኛል ደጁ
ተመችቶኛል ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ደጁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔስ (፪x) ያረፍኩት የተደላደልኩት
ሸክሜን በጌታ ላይ ጥዬ ቀና ብዬ የሄድኩት
ቀንበሬን ሰብሮታል የምን አንገት መድፋት
መንፈሱ ሲረዳኝ ሲሆንልኝ ስኬት
ከእንግዲህ ዓለመለስ እሄዳለሁ ወደፊት
ምርጫዬ ልክ ነው የዳንኩበት እውነት
አውጥቶ አይጥልም ሁሌ ይሸከማል
አያዋርድም ይልቅ ያከብራል
ክፉ ተናግሮ ማስቀየም አያውቅም
የፍቅር ቃሉ ተነግሮ አያልቅ
በሚያባባል ቃሎቹ ውስጤን አሳርፎታል
ደስ የሚያሰኘው ምክሩ ደግፎ አቁሞኛል
አዝማች · Chorus
ፍቅሩ በዛ ለእኔ ያደረገው መድህኔ
አላስችል አለኝ ላውጣ
ምላሽ ይሆን ዘንድ ላውራ
ይሄ ደጉ አምላክ ደጉ
ዝም አያሰኝም ፍቅሩ
አትታዘቡኝ ልጩህ ተመችቶኛል ደጁ
ተመችቶኛል ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ደጁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ተመችቶኛል ደጁ (፪x) (ተመችቶኛል (፪x))
ተመችቶኛል ደጁ (፪x) (ተመችቶኛል (፪x))
ተመችቶኛል (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ