ቀና አደረገኝ
Qena Aderegegne
2010 · ትራክ 11 · 5:52 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታ ነው (፪x) አሄ
ጌታ ነው ሊረዳኝ የደረሰው (፪x)
አዝማች · Chorus
ቀና አደረገኝ ቀና
እጄን በእጆቹ ያዘኛ
ከፍሎ ባሕሩን አሻገረኝ
እኔስ በጌታ አመለጥኩኝ (፪x)
አመለጥኩኝ እኔስ አመለጥኩኝ (፪x)
ጠላቴ እዚያው ሰጥሞ ቀረ
ኢየሱስ ብቻ ከበረ
ቁጥር 2 · Verse 2
አልቻልኩትም ብዬ ብዙ ያስቸገረኝን
ከእቅሜ በላይ ሆኖ ተራራ ያስገፋኝን
አንድ ግዜ ስጠራው ቃል ወጥቶ ከአፉ
የከበቡኝ ሁሉ ከአጠገቤ ጠፉ ተበተነ ሰልፉ
አዝማች · Chorus
ቀና አደረገኝ ቀና
እጄን በእጆቹ ያዘኛ
ከፍሎ ባሕሩን አሻገረኝ
እኔስ በጌታ አመለጥኩኝ (፪x)
አመለጥኩኝ እኔስ አመለጥኩኝ (፪x)
ጠላቴ እዚያው ሰጥሞ ቀረ
ኢየሱስ ብቻ ከበረ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለምንስ ልረበሽ የያዝኩት ሃይለኛ
ወጀቡ ቢበዛም አይደለም ሚተኛ
ልረጋጋ በቃ ጉልበቴ አይላላ
አጠገቤ ያለው አለው መፍትሄ መላ
አልይ ወደሌላ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቀና አደረገኝ ቀና
እጄን በእጆቹ ያዘኛ
ከፍሎ ባሕሩን አሻገረኝ
እኔስ በጌታ አመለጥኩኝ (፪x)
አመለጥኩኝ እኔስ አመለጥኩኝ (፪x)
ጠላቴ እዚያው ሰጥሞ ቀረ
ኢየሱስ ብቻ ከበረ
ቁጥር 4 · Verse 4
ቀና አደረገኝ (፪x) ቀና (፪x)
እጄን በእጆቹ ያዘና (፪x)
ባሕሩን ከፍሎ አሻገረኝ (፫x)
እኔስ በውዴ በጌታዬ አመለጥኩኝ (፪x)
አመለጥኩኝ (፬x)
አመለጥኩኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ