በተዓምራትህ
Betamerateh
2010 · ትራክ 9 · 5:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በተዓምራትህ እየተገረምኩ
በተዓምራትህ እየተደነቅኩ
ዛሬም ላመልክህ/ላለነግስህ መቅደስህ ገባሁኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይሄው የሽቶዬ መዓዛ
ይሽተት ማደሪያህን ይሙላ
ምክንያት አብዝቼ ላምልክ
ፍቅርህ ወሰን የለው ልክ (፭x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁልጊዜ ሁልጊዜ አዲስ ነህ አንተ ስትሰራ
ተነግሮ ተነግሮ አያልቅም ሥራህ ቢወራ (፪x)
ቀና ብዬ ሳይህ ትሆናለህ ልዩ
ተዓምር ስትሰራ ዓይኖቼ አንተን አዩ (፪x)
በአንደኛው (፪x) ስገረም ሌላኛው ሲመጣ
የአምላኬ የአድራጐቱ ብዛት ከውስጤ ሳይወጣ (፪x)
የአሰራሩ ሚስጥር ለእራሴ ሳይገባኝ
በኃያልነቱ ጌታ እኔን መራኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይሄው የሽቶዬ መዓዛ
ይሽተት ማደሪያህን ይሙላ
ምክንያት አብዝቼ ላምልክ
ፍቅርህ ወሰን የለው ልክ (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከፈተው ከፈተው አፌንም እንዳመሰግነው
አስችሎኝ እንዲሁ እንዳልቀመጥ ምክንያቴን አበዛው (፪x)
ብዙ እያደረገ ዛሬ ላይ አቆመኝ
በብቃቴ ሳይሆን በተዐምሩ አኖረኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይሄው የሽቶዬ መዓዛ
ይሽተት ማደሪያህን ይሙላ
ምክንያት አብዝቼ ላምልክ
ፍቅርህ ወሰን የለው ልክ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ