ደሙ
Demu
2010 · ትራክ 7 · 5:01 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስሬት ያለበት ፈውስ
አሮጌነትን ሽሮ የሚያደርግ አዲስ
በደልን ሊያስወግድ ፈፅሞ ኃይል ያለው
የጌታዬ ኢየሱስ ያ ክብሩ ደሙ ነው
አዝማች · Chorus
ደሙ ኃይል ጉልበቴ
ደሙ ሥር መሠረቴ
ደሙ ሆነኝ ብቃቴ
ደሙ መድኃኒቴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በደም የጠበቀ ቃልኪዳን ላይሻር
ሊፋቅ ሊደመሰስ ከቶ እንዳይሞከር
ስለገባው ጠላት በደም ተማምሎ
ሊገድለኝ ሊያጠፋኝ ጥርሶቹን አሹሎ
ወደ እኔ ሲመጣ በእራሱ ተማምሎ
የእኔ ጌታ ኢየሱስ በእኔ ቦታ ሆኖ
ያ የደምን ቃልኪዳን በደሙ አምክሮ
ሕይወት ሆነልኝ ነውሬን ሸፍኖ
አዝማች · Chorus
ደሙ ኃይል ጉልበቴ
ደሙ ሥር መሠረቴ
ደሙ ሆነኝ ብቃቴ
ደሙ መድኃኒቴ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሰሩት ኃጢያት ልክ ማሰሪያ እንዲሆን
ይሰዉ ነበረ የእንስሳቶችን ደም
አቅም ያለውማ ይሰረይለታል
መስዕዋት የሌለው እያነባ ይኖራል
አለ ግን በሰማይ የድሃ አደግ አባት
የሚራራ ሁሌ ለልጆቹ ሕይወት
መቅረብ እንዲችሉ ፊቱ በእኩልነት
ታሪክ ቀያየረ እርሱ ሆነ መስዕዋት
አዝማች · Chorus
ደሙ ኃይል ጉልበቴ
ደሙ ሥር መሠረቴ
ደሙ ሆነኝ ብቃቴ
ደሙ መድኃኒቴ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አስጠንቅቆት ነበር የሞትን መልዓክ
የእስራኤልን ሰፈር ከቶ እንዳይታወክ
የተነገረውም እንደዚህ እኮ ነው
ደንበር ላይ ካለ ትቶ እንዲያልፍ ነው
አዎ በእኔ መንደር መታወክ አይሆንም
አሳልፎ አይሰጠኝ የኢየሱሴ ደም
ዛሬም ተማምኜ ኮራ ብዬ እሄዳለሁ
በደም ነው የገዛኝ ዋጋዬ ውድ ነው
አዝማች · Chorus
ደሙ ኃይል ጉልበቴ
ደሙ ሥር መሠረቴ
ደሙ ሆነኝ ብቃቴ
ደሙ መድኃኒቴ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ