ድኛለሁ
Degnalehu
2012 · ትራክ 9 · 5:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንዴ ድኛለሁ ጽድቅን ጸድቄ
በከበረው ደም ከአብ ታርቄ
የቃልኪዳን ልጁ አድርጐኛል
ከእርሱ ፍቅር ማን ይለየኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
(ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ
ቁጥር 2 · Verse 2
በአንዱ አዳም ምክንያት ሞት ወደእኛ መጣ
አልታዘዝ ብሎ ከገነት ሊወጣ
አምላክ ሥጋ ለብሶ ወደምድር ወረደ
ራሱን ቤዛ አድርጐ ሊያጸድቀን ወደደ
አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ
እግዚአብሔር ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ
አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ
ሎሌ ሳልሆን ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ
ዘምሬ አልጠግብም ስለመዳኔ
ሌላው ሌላውማ ትርፍ ነው ለእኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
(ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ
ቁጥር 3 · Verse 3
አንዴ ድኛለሁ ጽድቅን ጸድቄ
በከበረው ደም ከአብ ታርቄ
የቃልኪዳን ልጁ አድርጐኛል
ከእርሱ ፍቅር ማን ይለየኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
(ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ
ቁጥር 4 · Verse 4
በማመኔ ብቻ ሳልደክም ሳልለፋ
ዘለዓለሜ አማረልኝ አምላክ ክብሩ ይስፋ
እውነትም መንገድም ሕይወትም እርሱ ነው
ኢየሱስ ያድናል ብዬ እመሰክራለሁ
አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ
እግዚአብሔር ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ
አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ
ሎሌ ሳልሆን ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ
ዘምሬ አልጠግብም ስለመዳኔ
ሌላው ሌላውማ ትርፍ ነው ለእኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
(ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ