ያኖራል
Yanoral
2012 · ትራክ 7 · 5:09 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ያኖራል የታመንኩት አምላክ
ያኖራል ተዐምር/ድንቅን እየሰራ
ያኖራል ተጸጽቼ አላውቅም
ያኖራል ሆኜ ከእርሱ ጋራ (፪x)
በበረሃው ላይ ምድረ በዳው ላይ
ምንጭን አፍልቆልኝ ጠጥቻለሁ
ከአስጨናቂው ጥሜ ረክቻለው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መከራው በዝቶ እንዴት ይኖራል እያሉ ሲያወሩ
እኔ ግን አለሁ እየዘመርኩኝ በዝቶልኝ ተዐምሩ (፪x)
ለታመነበት ጌታ ነው ለተደገፈው
ፍፁም አይጥልም አይረሳም ተስፋ ላደረገው (፪x)
አዝማች · Chorus
ያኖራል የታመንኩት አምላክ
ያኖራል ተዐምር/ድንቅን እየሰራ
ያኖራል ተጸጽቼ አላውቅም
ያኖራል ሆኜ ከእርሱ ጋራ (፪x)
በበረሃው ላይ ምድረ በዳው ላይ
ምንጭን አፍልቆልኝ ጠጥቻለሁ
ከአስጨናቂው ጥሜ ረክቻለው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ልዑል መጠጊያ ጥላ የሆነው
ሁሉን በእርሱ ጥሎ
ጻድቅ ሳይፈራ ልክ እንዳንበሳ
ያድራል . (1) . (፪x)
ሥሙ የጸና ግንብ ነው ዘመን የማይሽረው
ኢየሱስ ብሎ ያመልጣል ክፉ ሳይነካው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ