Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሳስበው

Sasebew

2012 · ትራክ 2 · 6:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳስበው (፫x) የአምላኬን ምህረት ቸርነቱን

ዘምር ያሰኘኛል እንደገና

በዋዛ ሚታለፍ መች ሆነና (፪x)

አላየውም እኔስ እንደዘበት

የማይገባኝን ክብር አይቻለሁ

ደግሜ ደግሜ ቸር ነህ ብለው

ፍቅር ነህ ብለው ፣ ደግ ነህ ብለው

ቃላት አጥቼ እንጂ

ይሄ ሁሉ ሲያንስ ነው (፬x)

ሞገስ ያገኘሁት አንተን አግኝቼ ነው ኢየሱሴ

የሰላሜ ምክንያት መሆንህን ታውቀዋለች ነፍሴ (፬x)

ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ

ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ

እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው

እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ

ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ

እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው

እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

ሳስበው (፫x) የአምላኬን ምህረት ቸርነቱን

ዘምር ያሰኘኛል እንደገና

በዋዛ ሚታለፍ መች ሆነና

አላየውም እኔስ እንደዘበት

የማይገባኝን ክብር አይቻለሁ

ደግሜ ደግሜ ክብሬ ነህ ብለው

ሞገሴ ብለው ፣ ማዕረጌ ብለው

ቃላት አጥቼ እንጂ

ይሄ ሁሉ ሲያንስ ነው (፬x)

ልቀኝልህ ቅኔ ብትወደኝ አይደል ወይ ሰው መሆኔ

ሰው ሁሉ ሲረሳኝ ያሰብከኝን አልረሳውም እኔ

አይተህ እንዳላየስ መች አለፍከኝ አልረሳውም እኔ

ከመንገድ ወድቄ ራራህልኝ አልረሳሁም እኔ

ቁስሌን ሳትጸየፍ ያከምክልኝ አልረሳውም እኔ

ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ

ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ

እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው

እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ

ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ

እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው

እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ