ምሥጋና
Mesgana
2012 · ትራክ 11 · 4:25 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፈረሱንና ፈረሰኛውን
በባሕር የጣለ እኛን አሻግሮን
በሚያስፈራ ግርማው ከፊት እየመራ
ነጥቆ ያስመለጠን ከዚያ ባለጋራ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትላንት የረዳን ያገዘን ጌታ
ዛሬም በዙፋኑ አለና እንጨምር ምሥጋና (፪x)
ብዙ ብዙ (ምሥጋና)
ከልባችን (ምሥጋና)
እንሰዋ (ምሥጋና)
ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)
ሌሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና
እስራኤልን የሚጠብቅ ለአፍታ ደክሞ አያውቅም
መንገድ አስጀምሮ ጥሎ የማይጠፋ
የማይሻር ኪዳን አለው ጽኑ ፍቅር ቀን ቢከፋ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደኃያልና እንደጨካኝ ወጥቶ
በሰልፉ ሜዳ ላይ ውጊያውን ተዋግቶ
ድል አድርጐ ባለድል ያደረገን እርሱ ነው
ይክበር ይንገሥልን ወደን እናምልከው ፈቅደን እናምልከው
አዝማች · Chorus
ትላንት የረዳን ያገዘን ጌታ
ዛሬም በዙፋኑ አለና እንጨምር ምሥጋና (፪x)
ብዙ ብዙ (ምሥጋና)
ከልባችን (ምሥጋና)
እንሰዋ (ምሥጋና)
ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)
ሌሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና
እስራኤልን የሚጠብቅ ለአፍታ ደክሞ አያውቅም
መንገድ አስጀምሮ ጥሎ የማይጠፋ
የማይሻር ኪዳን አለው ጽኑ ፍቅር ቀን ቢከፋ
ቁጥር 3 · Verse 3
ብዙ ብዙ (ምሥጋና)
ከልባችን (ምሥጋና)
እንሰዋ (ምሥጋና)
ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ