ተገልጦልኛል
Tegeltolegnal
2012 · ትራክ 12 · 5:42 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እውነት ተገልጦልኛልና ወደኋላ አልመለስም (፪x)
በአለማወቅ የኖርኩባቸው ዘመናቶቼ
ዳግመኛ እንዳላያቸው በአምላኬ እረሳኋቸው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጸያፍ ነበረ ምግባሬ በደሌም በዝቶ ነውሬ
እርሱ ባይረዳኝ ረድኤቴ አክትሞ ነበር ሕይወቴ
ከገደል አፋፍ መለሰኝ የሞትን ጽዋ ሳልቀምሰው
እራርቶልኛል በፍቅሩ ምሥጋና ክብር ይድረሰው
ለአምላኬና ለሥሙ ክብር
ስዘምር ውዬ ስዘምር ባድር
ለአምላኬማ አይገልጽልኝም
የውስጥ የልቤን ያለኝን ፍቅር (፪x)
አዝማች · Chorus
እውነት ተገልጦልኛልና ወደኋላ አልመለስም (፪x)
በአለማወቅ የኖርኩባቸው ዘመናቶቼ
ዳግመኛ እንዳላያቸው በአምላኬ እረሳኋቸው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የጽድቅን መንገድ ስልሳውቀው
ጉዙው አድክሞኝ ዝያለሁ
እረፍት የሌለው እርካታ
ውሸት ነው የዓለም ደስታ
መውጣት መውረዱ መልፋቱ
እርባን አቢስ ነው ሁሉ ከንቱ
ዓይኖቹ በርተው ላየው ሰው
የኢየሱስ መሆን መታደል ነው
ለአምላኬና ለሥሙ ክብር
ስዘምር ውዬ ስዘምር ባድር
ለአምላኬማ አይገልጽልኝም
የውስጥ የልቤን ያለኝን ፍቅር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ