ለውጠኝ
Lewetegn
2012 · ትራክ 5 · 5:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማደግ እሻለሁ አንተን መምሰል
ግን አቅቶኛል ክብሬን መጣል
የዚህ ዓለም ነገር ልቤን አድክሞት
ለአንተ እንዴት ልኖር ለሌላው ሳልሞት
የዚህ ዓለም ነገር ልቤን አዝሎት
ለአንተ እንዴት ልኖር ለሌላው ሳልሞት
ቁጥር 2 · Verse 2
ለውጠኝ (፫x) ለውጠኝ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው አያለሁ ልብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ (፪x)
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ (፪x)
ከካቻምና የአምና ከአምናው የዘንድሮ
ሕይወቴ ካልታየ ስምህ በእኔ ከብሮ
መኖርስ ምንድንነው ዘመን ማስቆጠሩ
እንዲያው መመላለስ ፍሬን ሳያፈሩ
አዝማች · Chorus
ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው አያለሁ ልብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ (፪x)
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የእምነት አባቶቼ አንተን አስከብረው
የክብርን ሞት አዩ በእምነታቸው ጸንተው
ፀጋህን አልብሰኝ አልኑር ተሸንፌ
ከሚጠፋው ዓለም ጸጸትን አትርፌ
አዝማች · Chorus
ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው አያለሁ ልብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ (፪x)
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ