Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እናያለን

Enayalen

2012 · ትራክ 6 · 5:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ይሰራል ይሰራል ምንስ ይሳነዋል

እግዚአብሔር ይሰራል ይሰራል ምንስ ያቅተዋል

የፈረሰው ቅጥር ታድሶ

እምባችን ከዓይናችን ታብሶ (፪x)

እናያለን እናያለን እናያለን

በነቢያቱ አፍ የተነገረው

የትንቢቱን ቃል እንወርሳለን (፪x)

በእግዚአብሔር ሰዎች የተባለውን

የትንቢቱን ቃል እንወርሳለን

የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ ያለ

ታማኝ ነው እርሱ ይችላል ንጉሡ

የቀድሞውን ግብር በእጥፍ እንዲመልስ በእራሱ የማለ

ታማኝ ነው እርሱ ይችላል ንጉሡ (፪x)

ታማኝ ነው እርሱ (ይችላል ንጉሡ) (፬x)

ምርኮ ተመለሰ ተመለሰ (፪x)

የጠላት መቆሚያ መሰዊያው ፈረሰ

ምርኮ ተመለሰ ተመለሰ (፪x)

የጠላት መቆሚያ መርገጫው ፈረሰ

እግዚአብሔር ይሰራል ይሰራል ምንስ ይሳነዋል

እግዚአብሔር ይሰራል ይሰራል ምንስ ያቅተዋል

የፈረሰው ቅጥር ታድሶ

እምባችን ከዓይናችን ታብሶ (፪x)

እናያለን እናያለን እናያለን

በነቢያቱ አፍ የተነገረው

የትንቢቱን ቃል እንወርሳለን (፪x)

በእግዚአብሔር ሰዎች የተባለውን

የትንቢቱን ቃል እንወርሳለን

የገሃነም ደጆች የማይቋቋሟት ታላቅ የቀደሳት/የመረጣት

ንጉሧ ነግሶ ሲገለጥባት

ዝናዋ ሞገሷ ከዳር ዳር ሲወጣ ስትሆን ገናና

ይህን በዓይናችን እናያለን ገና (፪x)

ዝማሬ ገኖ (እናያለን ገና)

ምድርን ሲሞላ (እናያለን ገና)

ተስፋን የሰጠው (እናያለን ገና)

ታማኝ ነውና (እናያለን ገና)

ምርኮ ተመለሰ ተመለሰ (፪x)

የጠላት መቆሚያ መሰዊያው ፈረሰ

ምርኮ ተመለሰ ተመለሰ (፪x)

የጠላት መቆሚያ መርገጫው ፈረሰ

ገና ገና እናያለን ገና...

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ