ክብርህን
Kebrehen
2012 · ትራክ 4 · 6:50 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሰው ምኞቱ ብዙ ነው
ሌት ተቀን በልቡ ሚያስበው
ዓይን ከማየት አይጠግብም
ጆሮም ከመስማት አይሞላም
እኔ ግን ክብርህን ማየት ነው ጥማቴ
ክብርህን ማየት ነው ጉጉቴ
በዚች ምድር ሳለች ሕይወቴ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ ሚያገኘውን ፈልጐ የመጣ
ከእጅህ ተቀብሎ ዳግመኛ ላይመጣ
እንደልቡ መሻት ሁሉን ብትሰጠው
አንተ ከሌለኸው ምንኛ ምስኪን ነው (፪x)
ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል
ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል
የዚህ ምድር ክብር መች ከልኩስ ያልፋል
ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል
አዝማች · Chorus
የሰው ምኞቱ ብዙ ነው
ሌት ተቀን በልቡ ሚያስበው
ዓይን ከማየት አይጠግብም
ጆሮም ከመስማት አይሞላም
እኔ ግን ክብርህን ማየት ነው ጥማቴ
ክብርህን ማየት ነው ጉጉቴ
በዚች ምድር ሳለች ሕይወቴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደሰው ወግ ልማድ ዓመታት ቆጥሬ
ማለፍ አልፈልግም ተራ ኑሮ ኖሬ
የተጠራሁለት የክብር ጥሪ ነው
ማቅለል አልፈልግም እንደዋዛ ላየው እንደቀልድ ላየው
ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል
ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል
የዚህ ምድር ክብር መች ከልኩስ ያልፋል
ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል
ለፍቶ ያከማቸው ጐተራው ሲሞላ
የማይቆርጠው ጥሙ ደግሞ ሲለው ሌላ
ሲባክን ይኖራል ርጋታን ፍለጋ
ከእረፍት ውኃ ምንጭ ቀርቦ ሳይጠጋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ