በድካሜ
Bedekamie
2012 · ትራክ 8 · 6:56 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኃይልህ በድካሜ ተገልጦ ስትሰራ አይቻለሁ
ከእኔ ምለው የለም የሆነው ይህ ሁሉ በአንተ ነው
ላከብርህ ዘንድ ይገባኛል ቸሩ አባቴ
ፊትህ ወድቄ ተንበርክኬ በጉልበቴ
ዝቅ ብዬ ላክብርህ
ታይብኝ ከፍ ብለህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደልጅ አይተኸኝ በልጅነት ወራት
ክፉ አመሌን ቻልከው የምህረትህ ብዛት
አልጨከንክብኝም እንድሰጥ ታልፌ
ስንቶችን ከመንገድ ካስቀረው ተርፌ
አለሁ በገናዬን ዛሬም አልሰቀልኩም
ስለቸርነትህ/ስለደግነትህ መዘመር አልተውኩን (፪x)
አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ጌታ ውለታህ ብዙ ነውና
አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ኢየሱስ ውለታህ ብዙ ነውና (፪x)
አዝማች · Chorus
ኃይልህ በድካሜ ተገልጦ ስትሰራ አይቻለሁ
ከእኔ ምለው የለም የሆነው ይህ ሁሉ በአንተ ነው
ላከብርህ ዘንድ ይገባኛል ቸሩ አባቴ
ፊትህ ወድቄ ተንበርክኬ በጉልበቴ
ዝቅ ብዬ ላክብርህ
ታይብኝ ከፍ ብለህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በውድቀቴ ስቀህ ጀርባ አልሰጠኸኝም
ዓይንህም እንዳየች አልበየንክብኝም
ይልቅ አስጠጋኸኝ መከርከኝ ለልቤ
ከቶ እንደማይበጅ ሰውኛው ሃሳቤ
ለተፍገመገመው ኃይልን የሰጠኸው
የሳተውን ደግሞ ቀርበህ የመለስከው
የእንደገና አምላክ አደረከኝ ቀና
ሃፍረቴን ሸፍነህ የቤቴን ገበና
አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ጌታ ውለታህ ብዙ ነውና
አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ኢየሱስ ውለታህ ብዙ ነውና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ