የካሳ ዘመን
Yekasa Zemen
2012 · ትራክ 1 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ሰማይ ምድር ይስማኝ ፍጥረት ያድምጠኝ
እግዚአብሔር ያሰበው ጸሎቱ የተሰማ ያ ሰው እኔ ነኝ
እኔ ነኝ"
ቁጥር 2 · Verse 2
በቆዘምኩበት ዘመን ፈንታ
ከፍ ሊያደርገኝ ደጉ ጌታ
መከራዬንም ሊያስረሳኝ
ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ
ባለቀስኩበት ዘመን ፈንታ
ደግሞ ሊያስቀኝ ደጉ ጌታ
መከራዬንም ሊያስረሳኝ
ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ
አዝማች · Chorus
የካሳ ዘመን አለ ከፊቴ (፪x)
ልውጣ ልውረሰው ወግድ ጠላቴ ዞርበል ጠላቴ
የበቀል ቅባት ስላረፈብኝ
ኪዳንህ ፈርሷል ዳግም ላትገዛኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወራሽ ሆኜ ሳለሁ እርስት እንደሌለው
የሃዘን የለቅሶ ቤቴን ልታደርገው
ወገን ዘመድ ያጣ ባይተዋር ብቸኛ
ብለህ ስትጣራ ጌታ መጣልኛ
በሰው አቆጣጠር ቢመስል የዘገየ
እውነተኛ ዳኛ መገፋቴን አየ
ጠላቴ ሆይ ስማ ብወድቅ እነሳለሁ
በጨለማ ብሄድ ጌታ ብርሃኔ ነው
የጠራኝ እግዚአብሔር አይጥልም አውቃለሁ
እንዳልሰማ የአንተን ስብከት
ውሸታም ነህ የውሸት አባት
ፈጣሪዬን ለእኔ ልታማ
ብዙ ሞከርክ መች ልታቅማማ
እኔስ የማውቀው ይሄን ነው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ለእኔ መልካም ነው (እግዚአብሔር ለእኔ መልካም) (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በቆዘምኩበት ዘመን ፈንታ
ከፍ ሊያደርገኝ ደጉ ጌታ
መከራዬንም ሊያስረሳኝ
ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ
ባለቀስኩበት ዘመን ፈንታ
ደግሞ ሊያስቀኝ ደጉ ጌታ
መከራዬንም ሊያስረሳኝ
ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ
አዝማች · Chorus
የካሳ ዘመን አለ ከፊቴ (፪x)
ልውጣ ልውረሰው ወግድ ጠላቴ ዞርበል ጠላቴ
የበቀል ቅባት ስላረፈብኝ
ኪዳንህ ፈርሷል ዳግም ላትገዛኝ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከላይ አዞልኛል የሰማይ አባቴ
ሞልቶ እንዲትረፈረፍ በበረከት ቤቴ
የሚያስፈልገኝን:ስለሚያውቅልኝ
ከእኔ ይልቅ ለእኔ የሚያስብልኝ
አምላክ አለኝና እጅግ ባለጠጋ
ለምንስ ልሳቀቅ እንዴት ብዬ ልሥጋ
ጠላቴ ሆይ ስማ ብወድቅ እነሳለሁ
በጨለማ ብሄድ ጌታ ብርሃኔ ነው
የጠራኝ እግዚአብሔር አይጥልም አውቃለሁ
እንዳልሰማ የአንተን ስብከት
ውሸታም ነህ የውሸት አባት
ፈጣሪዬን ለእኔ ልታማ
ብዙ ሞከርክ መች ልታቅማማ
እኔስ የማውቀው ይሄን ነው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ለእኔ መልካም ነው (እግዚአብሔር ለእኔ መልካም) (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ