እሄዳለሁ
Ehiedalehu
2013 · ትራክ 11 · 6:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማዕበሉ ለምን ገፋኝ አልልም ይግፋኝ
ወጀቡ ለምን ነካኝ አልልም ይንካኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
የአባቶቼ አምላክ ትናንት የረዳኝ
ዛሬም ነግሮኛል እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ማነው የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ አውሬው ሳይበላኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
እሄዳለሁ ማነው የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ አውሬው ሳይበላኝ (፪x)
ሁሉን ይችላል በእኔ ላይ (፫x)
የነፍሴ ጌታ አይደለም ወይ
ይችላል በእኔ ላይ (፪x)
ድንጋዩን ሁሉ እንቅፋቱን
ከፊቴ ጠርጐ ተራራውን
በእኔ ችሎ የማልችለውን
አለማምዶኛል ተዐምራቱን (፪x)
ማቆም ይችላል ማዕበሉን
ማዘዝ ይችላል ንፋሳቱን
ባያቆመውም አውራቂሱን
እሻገራለሁ ይዤ ቃሉን (፪x)
ቁዘማውን ይውሰደው
እርሱ የጠላቴ ንብረት ነው
ሞት አይሆንም በሕይወቴ
ገልብጦታል መድሃኒቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
የአባቶቼ አምላክ ትናንት የረዳኝ
ዛሬም ነግሮኛል እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ማነው የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ አውሬው ሳይበላኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚሆንለት እርሱ እንዳለው
የሚቆምለት እንዳሰበው
የዕድሜህን ቁጥር የሚያሰላው
የአባቶቼ አምላክ የእኔም ነው (፪x)
ስለዚህ ለምን ሽንፈትን ላውራ
ለትንሽ ነገር እንደተጠራ
ልታመን እንጂ ኃይል ባለው
ስሙ እግዚአብሔር በተባለው (፪x)
ቁዘማውን ይውሰደው
እርሱ የጠላቴ ንብረት ነው
ሞት አይሆንም በሕይወቴ
ገልብጦታል መድሃኒቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
የአባቶቼ አምላክ ትናንት የረዳኝ
ዛሬም ነግሮኛል እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ማነው የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ አውሬው ሳይበላኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ኦሮምኛ . (3) .
አዝማች · Chorus
የአባቶቼ አምላክ ትናንት የረዳኝ
ዛሬም ነግሮኛል እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ማነው የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ አውሬው ሳይበላኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ