ህዝቤን ስጠኝ
Hezbien Setegn
2013 · ትራክ 12 · 6:52 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታዬና አምላኬ አንተ የልቤ ሆይ (፪x)
አንዴ አስበኝና ማዳንህን ልይ (፪x)
ክንዱ ወዴት አለ ብሎ ለሚለኝ (፪x)
ለህዝብህ ጥያቄ ባክህ መልስ አርገኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ክብርህ ራበኝ (፪x)
አምላኬ ክብርህ ራበኝ
እንጀራ እንደሆነ ጠግቤያለሁኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የምድርን ቋጠሮ እባክህ ፍታልኝ (፪x)
ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ
የፈሰሰው እንባ ቢታበስ የፈረሰው ቅጥር ቢታደስ
ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ
ተራራው በፊትህ ቢናወጥ ስምህ ለጠላቶች ቢገለጥ
መልሰኛ ፈውስ አድርገህ ለሃገሬ ህመምተኛ
ቀድሰኛ እንድሆን የወንጌል አርበኛ
ተቆጥተህ ፊትህን አትደብቅብኝ
ደክሞኝ ሳለ ጠላቴ እንዳይወድቅብኝ
በፈረሰው ቅጥር የቆመ ለእንጀራ ያልኖረ (፪x)
የቤትህ ቅናት የሚበላው ስሙን የቀበረ (፪x)
የልብህን ቁጣ ትኩሳት የሚያበርድልህ (፪x)
እንዲህ ዐይነት ጨካኝ ሰው አድርገኝ ኃይልህን ሞልተህ (፪x)
ከዚያ በኋላማ ስምህን አክብረህ ትመላለሳለህ መስርአት ሳይከብድህ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ክብርህ ራበኝ (፪x)
አምላኬ ክብርህ ራበኝ
እንጀራ እንደሆነ ጠግቤያለሁኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
የህዝቤን/የምድሬን ቋጠሮ እባክህ ፍታልኝ (፪x)
ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ
የፈሰሰው እንባ ቢታበስ የፈረሰው ቅጥር ቢታደስ
ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ
ተራራው በፊትህ ቢናወጥ ስምህ ለጠላቶች ቢገለጥ
መልሰኛ ፈውስ አድርገህ ለሃገሬ ህመምተኛ
ቀድሰኛ እንድሆን የወንጌል አርበኛ
ተቆጥተህ ፊትህን አትደብቅብኝ
ደክሞኝ ሳለ ጠላቴ እንዳይወድቅብኝ
በምድሬ እንዳትሰራ እንዳትከብር የከለከልኩኝ (፪x)
አንካሳ የሕይወት ማንነት ያለኝ እኔ ነኝ (፪x)
አሁን ግን በምህረት ዐይንህ አይተኸኝ (፪x)
የተጨነቀውን ህዝብህን ስጠኝ (፪x)
ኢየሱስ እባክህ ነክቼህ ንካኝ
ኃይልህ እስኪወጣ ልበልህ ሙጥኝ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ክብርህ ራበኝ (፪x)
አምላኬ ክብርህ ራበኝ
እንጀራ እንደሆነ ጠግቤያለሁኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
የህዝቤን/የምድሬን ቋጠሮ እባክህ ፍታልኝ (፪x)
ህዝቤን ስጠኝ እንደፈቃድህ አውለኸኝ ህዝቤን ስጠኝ
ህዝቤን ስጠኝ በቅድስናህ አውለከኝ ህዝቤን ስጠኝ
ህዝቤን ስጠኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ