አልወርድም
Alwerdem
2013 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አስገረመኝ/አስደነቀኝ ነገሬን ውብ አረገና
አፌን ሞላው በአዲስ ቅኔ በምሥጋና
በዝማሬ እገባለሁ ወደ ቤቱ
ሥራዬ ተሰርቷልና በምረቱ
ኃይሌን አድሶት ጌታዬ ወጥቻለሁ አሃሃ ነቅቻለሁ
ከዚያ ላይ ማን ያወርደኛል ከፍ ብያለሁ አሃሃ ከፍ ብያለሁ
ጠላቴ አታገኘኝም በትላንቱ በትላንቱ
ኢየሱስ መጥቶ አውጥቶኛል በሰዓቱ በሰዓቱ
አዝማች · Chorus
በሰዓቱ በሰዓቱ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የማታ ለቅሶዬ ጠዋት ተለውጦ
እንደ መርደኪዮስ ታሪክ ነገር ተገልብጦ
በኮረብታ ሆኜ መዝሙር ዘምራለሁ ሆ
እኔ ከላይ ሆኜ ጠላቴን ረግጫለሁ
አልወርድም ከከፍታዬ ላይ
እግዚአብሔር አርጐኛል የበላይ
ዝቅታው ያንተ ነው ጠላቴ
እግዚአብሔር ጥሎሃል ከፊቴ
እግዚአብሔር ቀኑን እስኪሰጥ ድረስ
አይኔ ዝም ብሎ እምባን ቢያፈስ
እንዳለቀስኩኝ መቼ ቀረሁኝ
የምስቅበት ዘመን መጣልኝ
አዝማች · Chorus
አፌን ምሥጋና ኦሆ ይኸው ሞላኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አልወርድም ከከፍታዬ ላይ
እግዚአብሔር አርጐኛል የበላይ
ዝቅታው ያንተ ነው ጠላቴ
እግዚአብሔር ጥሎሃል ከፊቴ
የእግዚአብሔር ጉልበት የክንዱ ብርታት
ይህንን አድርጓል ሰርቶ ታምራት
ክፉ በሆኑት ቀናቶች ፈንታ
ደስታ አጠገበኝ ኤልሻዳዩ ጌታ
አመልከዋለሁ ሁሌ ጠዋት ማታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኃይሌን አድሶት ጌታዬ ወጥቻለሁ አሃሃ ነቅቻለሁ
ከዚያ ላይ ማን ያወርደኛል ከፍ ብያለሁ አሃሃ ከፍ ብያለሁ
ጠላቴ አታገኘኝም በትላንቱ ኦሆሆ በትላንቱ
ኢየሱስ መጥቶ አውጥቶኛል በሰዓቱ ኦሆሆ በሰዓቱ
በሰዓቱ በሰዓቱ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ልቤን አልጥልም ከጠፉት አህዮች ላይ
እግዚአብሔር መጥቷል ሊሰጠኝ ከዚያ በላይ
ሃሳቡ ለእኔ ምንጊዜም የመልካም ነው
ታምር ሲሰራ በሕይወቴ አይቻለሁ
አልወርድም ከከፍታዬ ላይ
እግዚአብሔር አርጐኛል የበላይ
ዝቅታው ያንተ ነው ጠላቴ
እግዚአብሔር ጥሎሃል ከፊቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ