Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከአፌ የማይጠፋው

Keafie Yemaytefaw

2013 · ትራክ 4 · 6:09 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከአፌ የማይጠፋ የማልረሳው የማልረሳው

ከአፌ የማይጠፋው የማልተወው የማልተወው

ከየት እንዳነሳኝ ነው (፬x)

አለኝ ብዙ ምሥጋና

ለጌታዬ አለኝ ብዙ ምሥጋና

ደግሜ ደግሜ እንደገና

ደግሜ ደግሜ እንደገና

ደግሜ ደግሜ እንደገና

ደግሜ ደግሜ እንደገና (፪x)

በሕይወት ለመኖር የሚያስችለኝ

ከሠማይ ትዕዛዝ ወጥቶልኝ

ነው እንጂ በቤቱ መሠንበቴ

መቼ በኃይልና በብርታቴ አሃ በብርታቴ

እርሱ ነው ከደሜ ያጠራኝ

አፍረቴን ሸፍኖ ያነሳኝ

እርቃኔን በመጎናጸፍያው

ደብቆ ያከበረኝ እርሱ ነው አሃ እርሱ ነው

ስለዚህ ጎትጓች አልፈልግም አምላኬን ለማመስገን ጌታዬን ለማመስገን

በእርሱ እኮ ነው የተሻገርኩት ያለፍኩት ያንን ክፉ ቀን (፪x)

አለኝ ብዙ ምሥጋና

ለጌታዬ አለኝ ብዙ ምሥጋና

ደግሜ ደግሜ እንደገና

ደግሜ ደግሜ እንደገና (፪x)

በንጉሥ ገበታ ተቀምጬ ከሕይወት እንጀራው እንድበላ

ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ይሁን ተብሎ ሲነገር ሲወራ (፪x)

በትልቁ እግዚአብሔር ተወድጄ ከውዳቂ ስፍራ ተነስቼ

በፊቱ ልቆም ዘንድ እኔ ማን ነኝ

እስከዚህ ነው ለካ የወደደኝ አሃሃ የወደደኝ

ስለዚህ ጎትጓች አልፈልግም አምላኬን ለማመስገን ጌታዬን ለማመስገን

በእርሱ እኮ ነው የተሻገርኩት ያለፍኩት ያንን ክፉ ቀን (፪x)

ከአፌ የማይጠፋ የማልረሳው የማልረሳው

ከአፌ የማይጠፋው የማልተወው የማልተወው

ከየት እንዳነሳኝ ነው (፬x)

አለኝ ብዙ ምሥጋና

ለጌታዬ አለኝ ብዙ ምሥጋና

ደግሜ ደግሜ እንደገና

ደግሜ ደግሜ እንደገና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ