እኔስ ኢየሱስ
Enies Eyesus
2013 · ትራክ 7 · 7:12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ህጉን ልተግብረው እንጂ በሕይወቴ ቃሉን ልኑረው
ያለኝ ሁሉ ይፈጸማል እግዚአብሔር ያለው
እራስ እንጂ ጅራት ላልሆን ቃሉ እንደሚለው
በስሙ የተጠራሁ ሰው ነኝ እኔ የኪዳኑ ሰው (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧረ እኔስ በኢየሱስ ክብር እንጂ
ያየሁት ውርደት አይደለም (፪x)
ገና እርሱ ያየልኝን አያለሁ
በሕይወቴ ጭንገፋ የለም
በሕይወቴ ጭንገፋ የለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እቸኩላለሁ ገና ገና ገና
ወደ ብዙ ክብር ገና
በዐይኔ አያለሁ ገና ገና ገና
የጌታን ተአምር ገናና (፪x)
እገሰግሳለሁ ወደ ፊትህ ፈጥኖ አንስቶኛል ከውድቀት
አልመለስም ወደኋላ እርፉን ይዣለሁ ላላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ላላይ ሌላ (፬x)
ክንዱን ተማምኖ እኔን ሲጠራ አሃሃ እኔን ሲጠራ (፪x)
ያልተጸጸተ በእኔ ሊሰራ አሃሃ በእኔ ሊሰራ (፪x)
መንገዴን ሁሉ አቅንቶልኛል አሃሃ አቅንቶልኛል (፪x)
ለብዙ ክብር ይፈልገኛል አሃሃ ይፈልገኛል (፪x)
ቃሉን ሊያጸና ሊደግፈኝ አሃሃ ሊደግፈኝ (፪x)
ከፊቴ ወጥቶ አይዞሽ ካለኝ አሃሃ አይዞሽ ካለኝ (፪x)
ታዲያ እንዴት ልፍራ ልኡሉን ይዤ አሃሃ ልኡሉን ይዤ (፪x)
ልጓደድ እንጂ ስሙን መዝዤ አሃሃ ስሙን መዝዤ (፪x)
እገሰግሳለሁ ወደ ፊትህ መቆም አልሻም መዘግየት
አልመለስም ወደኋላ እርፉን ይዣለሁ ላላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ላላይ ሌላ (፬x)
አዝማች · Chorus
ኧረ እኔስ በኢየሱስ ክብር እንጂ
ያየሁት ውርደት አይደለም (፪x)
ገና እርሱ ያየልኝን አያለሁ
በሕይወቴ ጭንገፋ የለም
በሕይወቴ ጭንገፋ የለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እቸኩላለሁ ገና ገና ገና
ወደ ብዙ ክብር ገና
በዐይኔ አያለሁ ገና ገና ገና
የጌታን ተአምር ገናና (፪x)
የሚዘጋና የሚከፍተው አሃሃ የሚከፍተው (፪x)
መወርወሪያውን የሰበረው አሃሃ የሰበረው (፪x)
ጠላቴን ሁሉ ተጣልቶልኛል አሃሃ ተጣልቶልኛል (፪x)
ተከናወኚ ሂጂ ብሎኛል አሃሃ ሂጂ ብሎኛል (፪x)
እንደመጣው ቃል አሜን ብያለሁ አሃሃ አሜን ብያለሁ (፪x)
ባሕር ተከፍሎ እሻገራለሁ አሃሃ እሻገራለሁ (፪x)
ሁሉን በሚያስችል ሁሉን እችላለሁ አሃሃ ሁሉን እችላለሁ (፪x)
እንዴት ብትሉ ኃይሌ የጌታ ነው አሃሃ ኃይሌ የጌታ ነው (፪x)
እገሰግሳለሁ ወደ ፊትህ መቆም አልሻም መዘግየት
አልመለስም ወደኋላ እርፉን ይዣለሁ ላላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ላላይ ሌላ (፬x)
አዝማች · Chorus
ኧረ እኔስ በኢየሱስ ክብር እንጂ
ያየሁት ውርደት አይደለም (፪x)
ገና እርሱ ያየልኝን አያለሁ
በሕይወቴ ጭንገፋ የለም
በሕይወቴ ጭንገፋ የለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ