የራራልኝ
Yeraralegn
2013 · ትራክ 2 · 6:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከልጅነቴ ጀምሮ እጄን አጥብቆ የያዘኝ
ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ በፍቅሩ ያባበለኝ
ጊንጡን ረጋግጦልኝ እባቡም እንዳይነድፈኝ
እንባዬን በእጁ ጠራርጐ አባት ልሁንሽ ያለኝ
አዝማች · Chorus
የራራልኝ የደገፈኝ ሰዎች ሲረሱኝ ያስታወሰኝ
ዛሬም ሊረዳኝ መች ይሰለቻል
በእርሱ ተረድቶ ማን ወድቆ ያውቃል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ
ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ
የሞተው ይነሳ የለም ወይ
ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ
ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ
አልአዛርስ ቆሞ የለም ወይ
በአመት መሃል ሁል ጊዜ የማይለወጥ ደግ ጌታ
ተስፋ ሲጨልም ቀን ሲመሽ የሚደርስ የማታ ማታ
ስሙን ጠርቼ አላፈርኩ አንገት አልደፋሁ በዘመኔ
ህያው ምስክር ያረገኝ ሳይርቀኝ ቆሞ ከጐኔ
አዝማች · Chorus
የራራልኝ የደገፈኝ ሰዎች ሲረሱኝ ያስታወሰኝ
ዛሬም ሊረዳኝ መች ይሰለቻል
በእርሱ ተረድቶ ማን ወድቆ ያውቃል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ
ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ
የሞተው ይነሳል የለም ወይ
ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ
ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ
አልአዛርስ ቆሞ የለም ወይ
የደረቀ አጥንት ነው ግን ለእግዚአብሔር ቀላል ነው
የሸተተ ሬሳ ነው ግን ለእግዚአብሔር ቀላል ነው
ትቼዋለሁ ቀብሬው ግን ለእግዚአብሔር ቀላል ነው
ያወጣዋል በጊዜው አዎ ለእግዚአብሔር ቀላል ነው
መርከብ ተሰብሮ በተሰበረው
መድረስ ከቻለ ያ የእምነት ሰው
ዛሬም በቤቴ ይሄ ይሆናል
አልጠረጥርም እርሱ ይችላል
አልጠረጥርም እርሱ ይችላል
አልጠረጥርም ጌታ ይችላል
አልጠረጥርም ጌታ ይችላል
አልጠረጥርም እርሱ ይችላል
አዝማች · Chorus
የራራልኝ የደገፈኝ ሰዎች ሲረሱኝ ያስታወሰኝ
ዛሬም ሊረዳኝ መች ይሰለቻል
በእርሱ ተረድቶ ማን ወድቆ ያውቃል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ