Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍጻሜ የሌለህ

Fetsamie Yelieleh

2013 · ትራክ 5 · 6:43 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍጻሜ የሌለህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

ዘለዓለም ነው ብዛትህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

የጸና ነው መንግሥትህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

ትገዛለህ በህይልህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

የማይፈራህ ማነው የማያከብርህ

ሁሉም ተንበርክኮ ይሰግዳል ፊትህ (፪x)

ስምህ የእግዚአብሔር ቃል አሜን የሆንከው

በምድር ክበባት ላይ የምትረግጠው

እንዲህን እንደዚያ የማትባለው

ታላቅነትህን እንዴት ልግለጸው (፪x)

ድንቅ ተዐምራትን በቃልህ የምትሰራ

የሌለውን ነገር በስም የምትጠራ

እስትንፋስን ሰጥተህ የምታኖረው

ያለና የሚኖር እንዳንተ ማነው (፪x)

ቅዱስ ቅዱስ ነህና (፫x)

ለስምህ ይሁን ምሥጋና (፬x)

የከበረ (ምሥጋና) ፣ የገነነ (ምሥጋና)

የገዘፈ (ምሥጋና) ፣ ብዙ የሆነ (መሥጋና)

የምትወደው (ምሥጋና) ፣ ምታሸተው (ምሥጋና)

ይሁንልህ (ምሥጋና) ፣ ሞገስ ያለው (ምሥጋና)

ፍጻሜ የሌለህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

ዘለዓለም ነው ብዛትህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

የጸና ነው መንግሥትህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

ትገዛለህ በህይልህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

የማይፈራህ ማነው የማያከብርህ

ሁሉም ተንበርክኮ ይሰግዳል ፊትህ (፪x)

የዘመንህ ቁጥር አየመረመር

የለህም ጓደኛ የሚፎካከር

በአመታት መሃል የማታረጅ ጌታ

ፍጥረት ይስገድልህ በጠዋት በማታ (፪x)

በገናው ይደርደር ከበሮው ይመታ

ምድር እልል ትበል ይነፋ እምቢልታ

በዜማ እቃ ሁሉ ስምህ ከፍ ይበል

ድንቅ መካር ጌታ ብርቱ ነህ ኃያል (፪x)

ቅዱስ ቅዱስ ነህና (፫x)

ለስምህ ይሁን ምሥጋና (፬x)

የከበረ (ምሥጋና) ፣ የገነነ (ምሥጋና)

የገዘፈ (ምሥጋና) ፣ ብዙ የሆነ (መሥጋና)

የምትወደው (ምሥጋና) ፣ ምታሸተው (ምሥጋና)

ይሁንልህ (ምሥጋና) ፣ ሞገስ ያለው (ምሥጋና)

ፍጻሜ የሌለህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

ዘለዓለም ነው ብዛትህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

የጸና ነው መንግሥትህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

ትገዛለህ በህይልህ አልፋ ኦሜጋ ነህ (፪x)

የማይፈራህ ማነው የማያከብርህ

ሁሉም ተንበርክኮ ይሰግዳል ፊትህ (፪x)

ቅዱስ ቅዱስ ነህና (፫x)

ለስምህ ይሁን ምሥጋና (፬x)

የከበረ (ምሥጋና) ፣ የገነነ (ምሥጋና)

የገዘፈ (ምሥጋና) ፣ ብዙ የሆነ (መሥጋና)

የምትወደው (ምሥጋና) ፣ ምታሸተው (ምሥጋና)

ይሁንልህ (ምሥጋና) ፣ ሞገስ ያለው (ምሥጋና)

ምሥጋና (፱x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ