Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስንት ጊዜ

Sent Gizie

2013 · ትራክ 10 · 4:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንድ ነገር በጣም ገብቶኛል በሕይወት ዘመኔ

የዛለው በአንተ ሲበረታ አይቻለሁ በዓይኔ

ተቆትተህ በዛው አትቀርም እስከ መጨረሻው

ቢወድቅም ይነሳል ፃዲቁ ስላለው መድረሻ

ስንት ጊዜ አነሳኸኝ

ስንት ጊዜ አቅም ሆንከኝ

ስንት ጊዜ ጨለማዬን

ከደንከው በብርሃን

ስንት ጊዜ ስደክምብህ

ስንት ጊዜ ያዘኝ ፀጋህ

ስንት ጊዜ ከጠላት ዛቻ

ከለለኝ ምህረትህ ብቻ (፭x)

ያንን ጭጋግ ደመናውን

ያን በረሃ ሃሩሩን

በአንተ ጉልበት አልፌዋለሁ

በማሳለፍ እንደ አንተ ማነው

ያን ኃጢያቴን ቁሻሻውን

ያንን ልብሴን እድፋሙን

ቀይረህ ከሞት ወጥቻለሁ

በማስወጣት እንደ አንተ ማነው

ስንት ጊዜ አነሳኸኝ

ስንት ጊዜ አቅም ሆንከኝ

ስንት ጊዜ ጨለማዬን

ከደንከው በብርሃን

ስንት ጊዜ ስደክምብህ

ስንት ጊዜ ያዘኝ ፀጋህ

ስንት ጊዜ ከጠላት ዛቻ

ከለለኝ ምህረትህ ብቻ (፭x)

ምህረትህ በዝቶልኝ ነው እንጂ ማነሳሳህ ደጋግሜ

በተከበበው ከተማማ ለእኔ ይገርመኛል መቆሜ

ስለዚህ በምሥጋና ልውጣ ያረክልኝን ቆጥሬ

ሳላስበው ከአንተ ጋራ አይቻለሁና ከብሬ

ስንት ጊዜ አነሳኸኝ

ስንት ጊዜ አቅም ሆንከኝ

ስንት ጊዜ ጨለማዬን

ከደንከው በብርሃን

ስንት ጊዜ ስደክምብህ

ስንት ጊዜ ያዘኝ ፀጋህ

ስንት ጊዜ ከጠላት ዛቻ

ከለለኝ ምህረትህ ብቻ (፭x)

አባትዬ ኢየሱስዬ

አልከሰርኩም እኔ አንተን ብዬ

እኔ አንተን ብዬ (፪x)

እኔ አንተን ብዬ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ