እስኪ አንድ ሰው
Eski And Sew
2013 · ትራክ 3 · 6:08 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አይቋረጥም ከጀመርኩት ምሥጋናዬ
እጨምራለሁ ከፍ ከፍ ይበል ጌታዬ
ይገባዋልና (፫x)
አይቋረጥም ከጀመርኩት ምሥጋናዬ
እጨምራለሁ ከፍ ከፍ ይበል ጌታዬ
ይገባዋልና (፫x)
እስቲ ለዚህ ጌታ አምልኮ ያለው (፬x)
ኢየሱስ በሕይወቱ የሆነው ብቸኛ
አመልካለሁ የሚል ቀኝ እጁን ይስጠኛ
ይተባበረኛ ይተባበረኛ
ቀኝ እጁን ይስጠኛ ፤ ቀኝ እጁን ይስጠኛ
ይተባበረኛ ይተባበረኛ
ቀኝ እጁን ይስጠኛ ፤ ቀኝ እጁን ይስጠኛ
አዝማች · Chorus
ከአመድ ላይ የተነሳ ታሪክ ያለው እንደኔ
ምሥጋና አለኝ የሚል ካለ ይቁምልኝ ከጐኔ
ክብሬን ስሜን ብጥልልህ እብድ አትበሉኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከጠላቴ ጽኑ እስርአት የተፈታሁ ነኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ አትታዘቡኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ ዝም በይ አትበሉኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ አትታዘቡኝ (፪x)
አሃሃሃ እስቲ አንድ ሰው የተደረገለት
አሃሃሃ ድቅድቅ ጨለማው የተገፈፈለት
አሃሃሃ እድፋሙ ልብሱ የተቀየረለት
አሃሃሃ ሃማ እያየ የተፈረደለት
አዝማች · Chorus
ከአመድ ላይ የተነሳ ታሪክ ያለው እንደኔ
ምሥጋና አለኝ የሚል ካለ ይቁምልኝ ከጐኔ
ክብሬን ስሜን ብጥልልህ እብድ አትበሉኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከጠላቴ ጽኑ እስራት የተፈታሁ ነኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ አትታዘቡኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ ዝም በይ አትበሉኝ
እኔ አለበኝ ውለታው እኔ አለብኝ
እኔ አለብኝ ውለታው ዝምበል አትበሉኝ (፪x)
አሃሃሃ እስቲ አንድ ሰው ፀሐይ የወጣለት
አሃሃሃ የተማሰ ጉድጓድ የተደፈነለት
አሃሃሃ ሟርቱ ድግምቱ የተረገጠለት
አሃሃሃ ብርቱ እግዚአብሔር የተሟገተለት
አዝማች · Chorus
ከአመድ ላይ የተነሳ ታሪክ ያለው እንደኔ
ምሥጋና አለኝ የሚል ካለ ይቁምልኝ ከጐኔ
ክብሬን ስሜን ብጥልልህ እብድ አትበሉኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ከጠላቴ ጽኑ እስራት የተፈታሁ ነኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ አትታዘቡኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ ዝም በይ አትበሉኝ
አሃሃሃ እስቲ አንድ ሰው ውለታ ያለበት
አሃሃሃ ሰባራ ልቡ የተጠገነለት
አሃሃሃ ሞቱ ሲታወጅ ትንሳኤ የሆነለት
አሃሃሃ ጌታ ነገሩን የገለበጠለት
አዝማች · Chorus
ከአመድ ላይ የተነሳ ታሪክ ያለው እንደኔ
ምሥጋና አለኝ የሚል ካለ ይቁምልኝ ከጐኔ
ክብሬን ስሜን ብጥልልህ እብድ አትበሉኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ከጠላቴ ጽኑ እስራት የተፈታሁ ነኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ አትታዘቡኝ
የእርሱ ውለታ አለብኝ የእርሱ ውለታ
የእርሱ ውለታ አለብኝ ዝም በይ አትበሉኝ
አይቋረጥም ከጀመርኩት ምሥጋናዬ
እጨምራለሁ ከፍ ከፍ ይበል ጌታዬ
ይገባዋልና ይገባዋልና
እስቲ ለዚህ ጌታ አምልኮ ያለው (፬x)
ኢየሱስ በሕይወቱ የሆነው ብቸኛ
አመልካለሁ የሚል ቀኝ እጁን ይስጠኛ
ይተባበረኛ ይተባበረኛ
ቀኝ እጁን ይስጠኛ ፤ ቀኝ እጁን ይስጠኛ
ይተባበረኛ ይተባበረኛ
ቀኝ እጁን ይስጠኛ ፤ ቀኝ እጁን ይስጠኛ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ