Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ያመለጠ እኔ ነኝ

Yamelete Enie Negn

2013 · ትራክ 1 · 6:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እስሬን ጥብቅ አደረገና

ማረጂያውን ሳል አረገና

ጉድጓድ ምሶ ሲጠብቀኝ

ቀን ቀጥሮ ዋጥ ሊያደርገኝ

ያመለጠ እኔ ነኝ ያመለጠ (፬x)

እስሬን ጥብቅ አደረገና

ማረጂያውን ሳል አረገና

ጉድጓድ ምሶ ሲጠብቀኝ

ቀን ቀጥሮ ዋጥ ሊያደርገኝ

ያመለጠ እኔ ነኝ ያመለጠ (፬x)

ያን ለት ነው አድራሻዬ የተቀየረዉ

ያን ለት ነው ችግር ለቆኝ ትቶኝ : የሄደው

ያን ለት ነው ያ ከሳሼ ጉድ የፈላበት

ያን ለት ነው ደጉ ጌታ ቤት የገባበት

ያመለጠ እኔ ነኝ ያመለጠ (፬x)

ከሲኦል መትረፌ በኢየሱስ ማረፌ ይህ ካልገረመኝ

ከልዑሉ ጋራ በቀኝ መቀመጤ ካላስጨፈረኝ

ታዲያ ምን ይግረመኝ ከመትረፌ ሌላ ምን ያስጨፍረኝ

ደሙን ከፍሎ እኮ ነው የሕይወቴ ጌታ ኧረፍት የሰጠኝ

ዛሬም ይግረመኝ እንጂ ነገም ይግረመኝ

በእርሱ አይደለም ወይ ችግሬ/ጨለማው እጁን ያሰጠኝ (፪x)

ያመለጠ እኔ ነኝ ያመለጠ (፬x)

ያመለጠ እኔ ነኝ (፬x)

በጣም ደካማ ሰው ሸክም ያጐበጠኝ የከበደብኝ

እንዲያው ወዶኝ እንጂ መዳን ያልተገባኝ ሙት ሰው ነበርኩኝ

መች ምህረት ወድጄ ወይስ እሮጬ ነው ይህ የሆነልኝ

የቀደሰኝ ጌታ መርገሜን ሻረና በሕይወት ኑሪ አለኝ

ዛሬም ይግረመኝ እንጂ ነገም ይግረመኝ

በእርሱ አይደለም ወይ ችግሬ/ጨለማው እጁን ያሰጠኝ (፪x)

ያመለጠ እኔ ነኝ ያመለጠ (፬x)

እኔ ነኝ (፬x)

ዘንዶ የተወጋልኝ እሳቱ የጠፋልኝ

ከአፈር የተነሳሁኝ ጌታ ሞገስ የሆነኝ

ዘንዶ የተወጋልኝ እሳቱ የጠፋልኝ

ከአፈር የተነሳሁኝ ጌታ ሞገስ የሆነኝ

ያመለጠ እኔ ነኝ ያመለጠ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ