Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክብር ላምላክ እያሉ

Keber Lamlak Eyalu

ትራክ 8 · 3:38 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስሙ መላእክት ሲዘምሩ

ክብር ለአምላክ እያሉ

ሰላም ይሁን በምድር ላይ

አምላክ ሰውን ታርቋል

ደስ ይበላችሁ ዘምሩ

ድል ተገኘ ዕልል በሉ

መልዕክቱን አስተጋቡ

ክርስቶስ ኢየሱስ ተወልዷል

ስሙን መላዕክት ሲያውጁ

ክብር ለአምላክ እያሉ

ክርስቶስ የክብር ንጉሥ

ዘለዓለማዊ አምላክ

ከሰማያት ወረደ

ከድንግል ተወለደ

አምላክ ሥጋ ለበሰ

ሰው ሆኖ ተገለጠ

ከእኛም ጋር ተዛመደ

ክርስቶስ የእና አማኑኤል

ስሙን መላዕክት ሲያውጁ

ክብር ለአምላክ እያሉ

ምሥጋና ለሰላም ንጉሥ

በሥልጣን ለሚነግስ

ብርሃን ሕይወትን አመጣ

በማዳን ኃይል ተነሳ

ክብሩን ለሰው ልጁን ሰዋ

ሞትን ሻረ ትልቅ ስራ

. (1) .

ስሙን መላእክት ሲያውጁ

ክብር ለአምላክ እያሉ

ክብር...

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ