Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኦ ቅዱስ ሌት

O Qedus Liet

ትራክ 6 · 4:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኦ ቅዱስ ሌት ከዋክብት ያበራሉ

የአዳኛችን ልደት ስለሆነ

ዓለም በኃጢአት ውስት ስትጨማለቅ

መጣላት ተስፋዋን ስትጠብቅ

ግሩም ተስፋ ነፍሳቸውን ያረካል

ደስ ይበለን ንጋት ሆኖልናል

ስገዱለት የመላዕክቱን ድምጽ ስሙ

በቅዱሴ በክርስቶስ ልደት

ቅዱስ መዝሙር ለእርሱ አቅርቡለት

ኢየሱስ የተወለደበት ያ ዕለት

ከዋክብት በድምቀት ያበሩበት

ሃሌሉያ

በእምነት ኃይል በብርሃኑ ተመርተን

በደስታ ልብ እንይ ያንን ህጻን

የኮከቡ ብርሃን አይተው ሲሮጡ

ጥበበኞች ከሩቅ ሃገር መጡ

ህጻኑ ንጉሥ በበረት ተኝቷል

በችግር ወንድማችን ሆኗል

የእኛን ሃሳብ ድካማችንን ሁሉ

እርሱ ያውቃል ወድቀን እንስገድለት

የእኛ ንጉሥ ተወልዷል በበረት

በዚህ በገና ሰሞን የክርስቶስን ልደት ስናከብር

የእግዚአብሔርን ፍቅር የፍቅሩን ጥልቀት እናስተውላለን

በየትናውም ቦታ የምትኖሩ የእግዚአብሔር ወገኖች

ኑ ኑ ኑ አክብሩት

ሃሌሉያ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ