Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የምስራቹ ቃል

Yemeserachu Qal

ትራክ 9 · 4:31 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታህን አመስግን ክርስቲያን ተነሳ

ልብህን ከእጆችህ ጋር ወደ አምላክህ አንሳ

ኢየሱስ ተወልዷል ምስራች ተናገር

እግዚአብሔር አምላክህን አመስግን በመዝሙር

የምስራቹ ቃል በምድር ተሰማ

በከብቶች በረት ውስጥ ቤትለሄም ከተማ

ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ

ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ

የአዋጅ ነጋሪ ድምጽ በምድር ሲያስተጋባ

የነብያት ትንቢት ፍፁም ሳይዛባ

ኢየሱስ ተወልዷል ለሰው መዳን ሆኗል

ዕልል በል ተናገር የምስራቹን ቃል

የምስራቹ ቃል በምድር ተሰማ

በከብቶች በረት ውስጥ ቤትለሄም ከተማ

ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ

ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ

የቀደመው አዳም ቢሞት በሃጥያቱ

አምላክ አልተወንም አልቆበት ምህረቱ

አማኑኤል ተወልዷል ምድር ታስተጋባ

አመስግን በአፍህ በእጆችህ ጭብጨባ

የምስራቹ ቃል በምድር ተሰማ

በከብቶች በረት ውስጥ ቤትለሄም ከተማ

ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ

ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ (፪x)

የምስራቹ ቃል በምድር ተሰማ

በከብቶች በረት ውስጥ ቤትለሄም ከተማ

ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ

ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ