Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጥቅስ በእምነት

Teqs Bemnet

ትራክ 3 · 1:56 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ

እነሆም ፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ ፥

ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ መልአኩም እንዲህ አላቸው

እነሆ ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ፤

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና

ይህም ምልክት ይሆንላችኋል ፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ

ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ

ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ

መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው

እንግዲህ እስከ ቤተ-ልሔም ድረስ እንሂድ

እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ

ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ [1]

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ