ደስ ይበለን
Des Yebelen
ትራክ 2 · 3:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መላዕክት ዘመሩለት ሰማይም ደመቀ
ኢየሱስ መወለዱ ለድሆች ታወቀ
መንፈስ የጸለለው የከበረው ህጻን
መድህን ተወለደ ከኃጢአት ሊያወጣን
አዝማች · Chorus
ደስ ይበለን (፬x) (ደስ ደስ)
እንዘምር በዕልልታ
መቸገራችንን አይቶ ወረደልን ጌታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ድግስ አዘጋጅቶ የሰማዩ ንግሱ
በልጁ ጋበዘን ሃብታም ደሃ ሳይል
መዳን የሚወዱ ሁሉም ይገባሉ
ከዘለዓለም ሃሴት በእርሱ ያደርጋሉ
አዝማች · Chorus
ደስ ይበለን (፬x) (ደስ ደስ)
እንዘምር በዕልልታ
መቸገራችንን አይቶ ወረደልን ጌታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ደስ ደስ
ደስ ይበለን
ኢየሱስ በልባችን ዛሬ ተወለደ
ለእኛ ብቻ አይደለም እርሱን ለወደደ
ለተጠጋው ሁሉ መቸገሩን አይቶ
ዛሬም ይወለዳል ዘመኑን ጠብቆ
አዝማች · Chorus
ደስ ይበለን (፬x) (ደስ ደስ)
እንዘምር በዕልልታ
መቸገራችንን አይቶ ወረደልን ጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ