ምሥጋናዬ
Mesganayie
2011 · ትራክ 5 · 5:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምላኬ የምሥጋናን መስዋዕት ለአንተ እሰዋለሁ
አምላኬ ሰልፉን ለአንተ ትቼ እኔ እዘምራለሁ (፪x)
አይጓደልብህ ምሥጋናዬ ፣ አይጓደልብህ አምልኮዬ(፪x)
በሰልፉ መሃል ቆሜ እዘምራለሁ (፪x)
ሃዘን ለቅሶዬን ትቼ እዘምራለሁ (፪x)
እዘምራለሁ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በጭካኔ በትር በብዙ ቆሳስለው
ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ተጥለው
ጸጥታው ይሰፍናል ወትሩም ሲሆን ሌሊት
ያኔ ግን ይሰማል ቁስለኛው ሲያቃስት
ይጠበቅ ነበር ማቃሰታቸው
ግን ተቀየረ ሌሊት ድምጻቸው
ሁኔታን ትተው ሲያመሰግኑ
የጌታ ኢየሱስ ታየ ማዳኑ
ዘምር ዘምር ይለኛል ኢየሱስን ሳስበው
አመስግነው ይለኛል ኢየሱስን ሳስበው (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋናዬ ይጨምራል ገና
አምልኮዬ ይጨምራል ገና
ዝማሬዬ ይጨምራል ገና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ንጉሥ እዮሳፍጥ ጠላቶች ከበውት
ንግስናውን ሊሽሩ እርስቱን ሊነጥቁት
የአባቶቹ አምላክ ፊቱን ቢፈልገዉ
ሰልፍ የእኔ ነው ብሎ ልቡን አሳረፈዉ
ምሥጋናን ይዞ ወጣ አደባባይ
ድልን አገኘ በጠላቱ ላይ
የአምላክ ድብቅ ጦር ተንቀሳቀሰ
ጠላት እርስ በእርስ ተጨራረሰ
ቁጥር 3 · Verse 3
አላወራውም የጠላቴን ሰልፍ ሃይለኛ ብዬ
አላወራውም አላስተጋባም ምሥጋናን ጥዬ
(ልማዴ ነው) በምሥጋና ላይ ለአንተ መጨመር
(ልማዴ ነው) ሁኔታን ትቶ ለአንተ መዘመር
(ባህሌ ነው) በምሥጋና ላይ ሌላ መጨመር
(ባህሌ ነው) ሁኔታን ትቶ ለአንተ መዘመር
አዝማች · Chorus
ልማዴ ነው (፪x)
ባህሌ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ